Amazing News | Feb 02, 2015. 12:53 PM comments 23917 views 8 likes
እናት!!!(አንተ ምንም ሁን ምን : እናት ያው እናት ናት!!)
ከባስ ውስጥ ወርጄ ዋሌቴ ከኪሴ እንደተሰረቀ እንዳወቅኩ ክፉኛ ደነገጥኩ። ዋሌቴ ውስጥ ያን ያክል ብዙ የሚያስጨንቅ ነገር አልነበረም። ውስጡ የነበረው 200 ብር እና ለእናቴ የጻፍኩት ደብዳቤ ብቻ ነበር። ደብዳቤው አጭር ሆኖ «እማዬ እንዴት አለሺልኝ። እኔ ደህና ነኝ። ከስራ ስላሰናበቱኝ በዚህ ወር ለገና እንኳን የምልክልሽ ብር የለኝም። እስከዚያ የሆነ ነገር ካገኘው ልክልሻለሁ።» የሚል ነበር።
ነገር ግን እናቴ ይሄንን ስታነብ የሚፈጠርባትን ሃዘን አስቤ አንድ ሳምንት ሙሉ በኪሴ ይዤው ዞሬአለሁ። 200 ብሩም ቢሆን ያን ያክል ትልቅ ብር አልነበረም . . . ግን በዚህ የኑሮ ውድነት ባሳበዳት ከተማ . . . ለእንደኔ አይነት እናቱን መርዳት ላለበት ሥራ አጥ . . .ሁለት መቶ ብሩ እንደ ሁለት ሺህ ብር ነበር።
ከትንሽ ቀናት በኋላ ከእናቴ አንድ ደብደቤ ደረሰኝ። ገንዘብ ላክልኝ ልትለኝ ነው በሚል ተሳቅቄ እና ፈርቼ ቀኑን ሙሉ ሳልከፍተው ይዤው ስዞር ዋልኩ። ማታ ላይ ከፍቼ አነበብኩት። ክው!! ነው ያልኩት። እናቴ የላከችልኝ ደብዳቤ «ልጄ የላክልኝ 500 ብር ደርሶኛል። ቀን ይውጣልህ። የምትሰጠው አያሳጣህ።» የሚል ነበር። ማን ይሆን ገንዘቡን የላከላት ብዬ ዝም ብዬ ሳስብ አድሬ በማግስቱም ሳስብ ዋልኩ።
ጥቂት ቀናት አለፉ። ከእናቴ ሌላ ደብዳቤ ደረሰኝ። «ልጄ፤ ከገንዘቡ ጋር የላክልኝ ደብዳቤ ደቃቅ እና የማይነበብ አይነት ፅሁፍ ሆኖብኝ አላነበብኩትም። መነጽሬም ባለፈው እንጀራ ስጋግር ወድቆ ስለተሰበረ ማንበብ አልቻልኩም። የጋሽ በቀለ ልጅ ሲመጣ በሱ መልሼ ላኩልህ።» የሚል ነበር ደብደቤው። እኔ ደብዳቤም ሆነ ገንዘብ አልላኩላትም ነበር።
ብቻ የተላከውን ደብዳቤ ከፍቼ ሳነበው እንዲህ ይላል፦«ለእናትህ 500 ብር ልኬላቸዋለሁ - ያንተ 200 ብር ላይ የራሴን 300 ብር ጨምሬ። ምንም ቢሆን እናት እናት ነች። መራብ የለባትም። ለማንኛውም በተቻለህ ፍጥነት ስራ ፈልግና እናትህን ተንከባከባቸው። ያንተው ኪስ አውላቂ።»
እኛ ምንም አንሁን ምን፤ እናት ግን እናት ናት።
ኮፒ ራይት:- እያዩ ክሊኒክ / Eyayu Clinic የፌስቡክ ፔጅ/ገጽ (እናመሰግናለን!)
እናት!!!
(አንተ ምንም ሁን ምን : እናት ያው እናት ናት!!)
ከባስ ውስጥ ወርጄ ዋሌቴ ከኪሴ እንደተሰረቀ እንዳወቅኩ ክፉኛ ደነገጥኩ። ዋሌቴ ውስጥ ያን ያክል ብዙ የሚያስጨንቅ ነገር አልነበረም። ውስጡ የነበረው 200 ብር እና ለእናቴ የጻፍኩት ደብዳቤ ብቻ ነበር። ደብዳቤው አጭር ሆኖ «እማዬ እንዴት አለሺልኝ። እኔ ደህና ነኝ። ከስራ ስላሰናበቱኝ በዚህ ወር ለገና እንኳን የምልክልሽ ብር የለኝም። እስከዚያ የሆነ ነገር ካገኘው ልክልሻለሁ።» የሚል ነበር።
ነገር ግን እናቴ ይሄንን ስታነብ የሚፈጠርባትን ሃዘን አስቤ አንድ ሳምንት ሙሉ በኪሴ ይዤው ዞሬአለሁ። 200 ብሩም ቢሆን ያን ያክል ትልቅ ብር አልነበረም . . . ግን በዚህ የኑሮ ውድነት ባሳበዳት ከተማ . . . ለእንደኔ አይነት እናቱን መርዳት ላለበት ሥራ አጥ . . .ሁለት መቶ ብሩ እንደ ሁለት ሺህ ብር ነበር።
ከትንሽ ቀናት በኋላ ከእናቴ አንድ ደብደቤ ደረሰኝ። ገንዘብ ላክልኝ ልትለኝ ነው በሚል ተሳቅቄ እና ፈርቼ ቀኑን ሙሉ ሳልከፍተው ይዤው ስዞር ዋልኩ። ማታ ላይ ከፍቼ አነበብኩት። ክው!! ነው ያልኩት። እናቴ የላከችልኝ ደብዳቤ «ልጄ የላክልኝ 500 ብር ደርሶኛል። ቀን ይውጣልህ። የምትሰጠው አያሳጣህ።» የሚል ነበር። ማን ይሆን ገንዘቡን የላከላት ብዬ ዝም ብዬ ሳስብ አድሬ በማግስቱም ሳስብ ዋልኩ።
ጥቂት ቀናት አለፉ። ከእናቴ ሌላ ደብዳቤ ደረሰኝ። «ልጄ፤ ከገንዘቡ ጋር የላክልኝ ደብዳቤ ደቃቅ እና የማይነበብ አይነት ፅሁፍ ሆኖብኝ አላነበብኩትም። መነጽሬም ባለፈው እንጀራ ስጋግር ወድቆ ስለተሰበረ ማንበብ አልቻልኩም። የጋሽ በቀለ ልጅ ሲመጣ በሱ መልሼ ላኩልህ።» የሚል ነበር ደብደቤው። እኔ ደብዳቤም ሆነ ገንዘብ አልላኩላትም ነበር።
ብቻ የተላከውን ደብዳቤ ከፍቼ ሳነበው እንዲህ ይላል፦
«ለእናትህ 500 ብር ልኬላቸዋለሁ - ያንተ 200 ብር ላይ የራሴን 300 ብር ጨምሬ። ምንም ቢሆን እናት እናት ነች። መራብ የለባትም። ለማንኛውም በተቻለህ ፍጥነት ስራ ፈልግና እናትህን ተንከባከባቸው። ያንተው ኪስ አውላቂ።»

Comments