የ2014 የዓለም ዋንጫ እውነታዎች MUST READ -


 

የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ እውነታዎች – ይህን ሳያነቡ ጨዋታው እንዳይጀመር!

(ሰንደቅ ጋዜጣ)

በየአራት አመቱ የሚካሄደው ተወዳጁ የእግር ኳስ ስፖርት መድረክ፣ የአለም ዋንጫ የአለም ደረስኩ ደረስኩ እያለ ነው። ብራዚል ለሁለተኛ ጊዜ የምታስተናግደው 20ኛው የአለም ዋንጫ ሊጀመር አንድ ሳምንት ይቀረዋል። የስፖርቱ አፍቃሪ የአለም ህዝብ ሁሉ የውድድሩን መጀመር በታላቅ ጉጉት እየጠበቀ ነው። ተሳታፊ ሀገሮችም ወደ ደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር እያቀኑ ነው። 

በስምንት ምድብ የተደለደሉ 32 ብሔራዊ ቡድኖች ለአንድ ወር የሚያደርጉትን ፉክክር በብራዚል12 ከተሞች ይስተናገዳሉ። አስተናጋጇ ብራዚል ከክሮሺያ የምታደርገውን የመክፈቻ ጨዋታ በሳኦ ፖሎ አሬና ደ ሳኦፖሎ ወይም አሬና ኮሮንቲያስ ተብሎ በሚጠራው ስታዲየም ይካሄዳል። የፍጻሜው ጨዋታ ደግሞ በ1950 የአለም ዋንጫ ብራዚል በፍጻሜ ጨዋታ በኡራጓይ ተሸንፋ ዋንጫ ባጣችበት በሪዮ ዴ ጄኔሪዮ ከተማ በሚገኘው ግዙፉ ማራካኛ ስታዲየም ይስተናገዳል።
የ2014 የፊፋ የአለም ዋንጫ ለአንድ ወር ያህል ጊዜ ሲካሄድ አስገራሚ ክስተቶችም እንደሚታይበት ይጠበቃል። የአለም ዋንጫውን ከወዲሁ ልዩ የሚያደርጉት በርካታ እውነታዎችም እንዳሉ ይታወቃል። ከነዚህም መካከል የተወሰኑት በዚህ ጽሁፍ ተካተዋል።

በተቃውሞ ድምጾች የሚታጀብ የአለም ዋንጫ
በአለም ዋንጫ ሲቃረብ ታዲያ የአለም መገናኛ ብዙሀንን የሳበው እንደወትሮው በውድድሩ ሻምፒዮና የሚሆኑ ቡድኖችና ኮከብ ተጫዋቾች ጉዳይ አይደለም። ከሁሉም በላይ መነጋገሪያ የሆነው ውድድሩን የሚካሄድባቸው ስታዲየሞች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ መሰረት አለመጠናቀቃቸውና የአለም ዋንጫውን ከፍተኛ ወጪን የተቃወሙ ብራዚላውያን ጉዳይ ነው። የተቃውሞ ሰልፉ እየተጠናከረና እየተስፋፋ መምጣቱ የአለም ዋንጫውን ስኬታማነት ላይ ስጋት አሳድሯል።
የውድድሩ አዘጋጆች ግን ውድድሩ በታቀደው መሰረት በስኬት ይጠናቀቃል እያሉ ነው። የብራዚል መንግስትም ሆነ ፊፋ የአለም ዋንጫው ምንም እክል እንዳይገጥመው እናደርጋለን ቢሉም የሚሳካላቸው አይመስልም።
ሰሞኑን ከኳታር የ2022 የአለም ዋንጫ አዘጋጅነት ጋር በሙስና እየተብጠለጠለ የሚገኘው ፊፋ ለብራዚል ያለውን ጠንካራ ድጋፍ በተደጋጋሚ ገልጿል። ከሶስት አመት በፊት ጡረታ እንደሚወጡ ተናግረው የነበሩትና አሁን ደግሞ በቀጣዩ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እሳተፋለው ያሉት ሴፕ ብላተር ‹‹ሀገሪቱ ዝግጅቷ የተጓተተ ቢሆንም የአለም ዋንጫውን እንድታስተናግድ መመረጧ ግን ተገቢ ነው›› ብለዋል።
ይሁንንና የድግሱ ባለቤቶች ብራዚላውያን ከ50 አመት በኋላ ወደ ቤታቸው የመጣውን የአለም ዋንጫ በተወዳጁ የሳምባ ዳንሳቸው አድምቀው በክብር የሚቀበሉት አልሆኑም። ‹የኑሮ ውድነት ጣሪያ ነክቷል፣ የአለም ዋንጫ አሁን ላይ ዳቦ አይሆነንም› ያሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች አደባባይ ወጥተው ቅሬታቸውን እያሰሙ ነው። ‹‹ትበላው የላት ትከናነበው አማራት›› የሚለውን የኢትዮጵያውያን አባባል የሚያስታውሱ ብራዚላውያን ምሬቶች ጎልተው እየተሰሙ ነው። ብራዚላውያኑ ‹ትምህርት ቤቶችና የጤና ተቋማት፣ በቂ የመጓጓዣ አውቶብሶችና ባቡሮች ሳይኖሩን መንግስት ለአለም ዋንጫ ብሎ ስታዲየም በማሰራትና በማደስ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥቷል› ሲሉ ወቀሳቸውን ያሰማሉ። የአለም ዋንጫ መዘጋጀቱ ብቻ ሳይሆን ከሀገሪቱ ደሀ ዜጎች ላይ በግብር የሚሰበሰብ መሆኑ ነው ይበልጥ ያስቆጣቸው።
ብራዚላውያን ምንም እንኳን የእግር ኳስ ፍቅር በደማቸው ውስጥ የሰረጸ ቢሆንም የአለም ዋንጫ ለድህነት የሚዳርጋቸው ከሆነ አዘጋጅነቱ ወደ ምድራቸው ባይመጣ ይመርጣሉ። ከአመት በላይ የዘለቀው ተቃውሟቸውም የአለም ዋንጫው ሲጀመር እንደሚጋጋል ይጠበቃል። በይበልጥ ደግሞ ቡድናቸው ለፍጻሜ የማይደርስና በጊዜ የሚሰናበት ከሆነ የከፋ ትርምስ መፈጠሩ አይቀርም። ቡድናቸው ዋንጫ ቢወስድም እንኳ ተቃውሟቸውን ከመግለጽ እንደማያግዳቸው መገመት ይቻላል። ለዚህም ደግሞ በ2013 የኮንፌዴሽን ዋንጫ ቡድናቸው አሸንፎ እንኳ በመንግስት ላይ ቅሬታቸውን ከመግለጽ ያልተቆጠቡበትን አጋጣሚ ማስታወስ ተገቢ ነው።

የጎል መስመር ቴክኖሎጂ
ባለፉት ጊዜያት በአለም ዋንጫ መድረኮች ላይ በርካታና አይረሴ አወዛጋቢ የጎል ውሳኔዎች ታይተዋል። በብራዚሉ የአለም ዋንጫ ግን መሰል ድርጊት አይኖርም። የጎል መስመር ቴክኖሎጂ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ የሚሆንበት የመጀመሪያው የአለም ዋንጫ ይሆናል። በአለም ዋንጫው ወቅት አርቢትሮች በስታዲየሙ ዙሪያ በተገጠሙ 14 ካሜራዎችና ኮምፒውተር ቴክኖሎጂ እየታገዙ ጎል መቆጠሩን ያረጋግጣሉ። ይኸውም ለግብነት የተሞከረች ኳስ የግብ መስመሩን የምታልፍ ከሆነ አርቢትሮች እጃቸው ላይ በሚያስሩት ልዩ ሰአት አማካኝነት ንዝረት ይሰማቸዋል። ‹ጎል› የሚል የዕሁፍ መልዕክትም ይታያቸዋል።
ሌላው በብራዚሉ የአለም ዋንጫ ተግባራዊ የሚሆነው ቴክኖሎጂ በስታዲየም ውስጥ ደህንነትንና ጸጥታን ከማስጠበቅ ጋር በተያያዘ የሚሰማሩ ሮቦቶች መኖራቸው ነው። ሮቦቶቹ የደህንነት ስጋት የሚሆኑ ክስተቶችን አስቀድመው የሚጠቁሙ ማንቂያ ምልክቶችና ድምጾችን የሚያመለክቱ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም በስታዲየሙ ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ እንቅስቃሴዎችንና ረብሻዎችን መቆጣጠር የሚችሉ ሮቦቶች ይሰማራሉ። እነዚህ ሮቦቶች በስታዲየም ፖሊሶችን ስራ እንደሚያቀሉ ታምኖባቸዋል።

ውዱ የአለም ዋንጫ መድረክ
የብራዚሉን የ2014 የአለም ዋንጫ ለየት ከሚያደርጉት እውነታዎች መካከል ዋንኛው እስከ አሁን ከተካሄዱ የአለም ዋንጫዎች ሁሉ ከፍተኛ ወጪን በመጠየቅ ቀዳሚው መሆኑ ነው። ብራዚል ለአለም ዋንጫው ከ14 እስከ 16 ቢሊዮን ዶላር እንደሚፈጅባት ተነግሯል። ይኽም ወጪ ባለፉት ሶስት የአለም ዋንጫዎች አጠቃላይ ወጪ እጥፍ መሆኑ ነው። ከሁሉም በላይ ደግሞ ከፍተኛ ወጪ የተባለው ለስታዲየም ግንባታና እድሳት ከ1ቢለዮን ዶላር በላይ ያወጣችው ወጪ ነው። ገንዘቡ ደግሞ ከደሀው ህዝብ ከግብር የሚሰበሰብ መሆኑ ህዝቦቿን ለአደባባይ ተቃውሞ አብቅቷቸዋል።
የአለም ዋንጫው በዝግጅት ብቻ ሳይሆን በተለያዩ አገልግሎቶች በኩልም ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ መሆኑ ተጠቅሷል። በውድድሩ ወቅት የሆቴሎች፣ የምግብና መጠጥ እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶች ዋጋቸው የትየሌለ ነው ተብሏል። የአለም ዋንጫውን ተከትሎ በብራዚል በሁሉም መስክ የሚሰጡ አገልግሎቶች ዋጋ በከፍተኛ መጠን ንሯል። በተለይም ውድድሩን ለመመልከት ከተለያዩ የአለም ክፍሎች ወደ ብራዚል የሚጓዙ ከ600ሺ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ ይጠብቃቸዋል።

የመክፈቻ ንግግር የሌለው የአለም ዋንጫ
የአለም ዋንጫ ውድድር ሁልግዜም በመክፈቻ ዝግጅቶች ይደምቃል። በክብር እንግዶች የመክፈቻ ንግግር አማካኝነትም ውድድሩ በይፋ መጀመሩ ይበሰራል። የብራዚሉ የ2014 የአለም ዋንጫ ግን ያለ መክፈቻ ንግግር ነው የሚጀመር መሆኑ ልዩ ያደርገዋል። ምክንያቱ ደግሞ የመክፈቻ ንግግር ሲደረግ የአለም ዋንጫውን የሚቃወሙ የብራዚላውያን ድምጾች እንዳይሰሙ ለማድረግ ነው።
ባለፈው አመት ብራዚል የኮንፌዴሬሽን ዋንጫን ስታዘጋጅ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዳይላማ ሩሴልፍና የፊፋው ፕሬዝዳን ሴፕ ብላተር የመክፈቻ ንግግር ሲያሰሙ ንግግራቸው በስታዲየሙ በነበሩ ብራዚላውያን የተቃውሞ ድምጽ ሊሰማ አልቻለም ነበር። በአለም ዋንጫው የመክፈቻ እለትም ብራዚላውያን መሰል የተቃውሞ ድምጽ እንደሚያሰሙ በመገመት ምንም አይነት የመክፈቻ ንግግር እንዳይደረግ ተወስኗል።

የቡድኖች ልዩ ፍላጎቶች
በአለም ዋንጫ የሚሳተፉ ብሔራዊ ቡድኖች ምቾታቸው እንዲጠበቅና ምንም ቅሬታ እንዳይሰማቸው አስተናጋጇ ሀገር የምትችለውን ሁሉ ጥረት ታደርጋለች። ለዚህም ተሳታፊ ቡድኖች በሚያርፉበት ሆቴል ውስጥ እንዲኖር የሚፈልጓቸው ነገሮችንና ሁኔታዎች እንዲያሳውቋት አስቀድማ ትጠይቃለች።
በብራዚሉ የአለም ዋንጫም ቡድኖች በሆቴላቸው ውስጥ እንዲሟሉላቸው የሚፈልጓቸው ነገሮች ተጠይቀው ምላሻቸውን አሳውቀዋል። አንዳንዶቹ ተገቢና ስሜት የሚሰጡ ሲሆን፣ አግራሞትን የሚፈጥሩም ይኖራሉ። አርት52 የተሰኘ የእንግሊዝ ድረገጽ አስገራሚ ካላቸው የብሔራዊ ቡድኖች ፍላጎቶች ያላቸውን ጠቅሷል። በቀዳሚነትም የኡራጓይ ቡድን ልዩ ፍላጎትን ጽፏል። ሞቃታማው የብራዚል የአየር ንብረት ያሳሰበው የኡራጓይ ብሔራዊ ቡድን በሆቴሉ ውስጥ ምንም ድምጽ የሌለው አየር ማቀዝቀዛ እንዲኖር ጠይቋል።
የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ደግሞ በሆቴሉ ውስጥ ኮምፒውተሮች እንዲሟሉለት የጠየቀ ሲሆን፣ ጃፓኖች ጃኩዚ በእያንዳንዱ መኝታ ክፍል ውስጥ እንዳይቀርብን ብለዋል። አልጄሪያዎች ቅዱስ ቁርአን በሆቴላቸው ውስጥ ማግኘት እንደሚፈልጉ አሳውቀዋል።
የማንቸስተር ሲቲውን ቅንጡ አማካኝ ተጫዋች ሳሚር ናስሪን ያላካተተው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ደግሞ በበሆቴል ውስጥ ለአባላቱ ደረቅ ሳሙና ሳይሆን ፈሳሽ ሳሙና ብቻ እንሚፈልግ አስታውቋል። ኢኳዶራውያን ደግሞ በእያንዳንዱ ክፍላቸው ውስጥ ሁሌም ሙዝ ማጣት እንደማይፈልጉ ነው የገለጹት።

Source ሰንደቅ ጋዜጣ
Comment Box is loading comments...

Comments

Other posts you may likeFunny Zenjero
Funny Zenjero
picture
7175 views 5 likes
Zaki Magna Kemegenagna New Motor Bike Funny
Zaki Magna Kemegenagna...
picture
8237 views 2 likes
We Are Producing Bike
We Are Producing Bike
picture
3861 views 2 likes
ሃሃሃሃ..ታብሌት Vs ወረቀት Very Funny
ሃሃሃሃ..ታብሌት Vs ወረቀት Ver...
video
6466 views 18 likes
Be Kind To Each Other
Be Kind To Each Other
picture
3311 views 3 likes
ያንዲት አሜሪካዊ ድመት ጸሎት Funny
ያንዲት አሜሪካዊ ድመት ጸሎት Fun...
picture
9801 views 14 likes
Why Bananas Turn Black Funny
Why Bananas Turn Black...
picture
6521 views 1 likes
አማርኛ Joke Of The Week #38
አማርኛ Joke Of The Week ...
picture
15062 views 6 likes
We Are In Love
We Are In Love
picture
7390 views 12 likes
Kikiki Lol ሚስ ውሻ
Kikiki Lol ሚስ ውሻ
video
3795 views 3 likes
Valentine After  ትዳር
Valentine After ትዳር
picture
14342 views 11 likes
IRON MAN ETHIOPIA FUNNY
IRON MAN ETHIOPIA FUNN...
picture
12309 views 3 likes