የአለቃ ገብረሐና 71 ቀልዶች part 1 -


ሃድጎ -አህያ ሸራህያ 1. ጋዜጠኛው አረፋይኔ ሀጎስ ስለ አለቃ ገብረ ሃና መጽሀፍ ጽፏል። ታዲያ አለቃ ከአጼ ተዎድሮስ ጊዜ ጀመሮ የነበሩ የቤተክርስቲያን ምሁር እንደሆኑ ነው መጽሀፉ የሚያወራው።ከጊዜው ቀልዳቸው አንዱ እንዲህ ይላል። በአጼ ተዎድሮስ ቤተመንግስት ሀድጎ የሚባል ባለሟል ነበረ ታዲያ ምንም እንኳን ንጉሱ ቀልድ የማያውቁ ኮስታራ ቢሆኑም አለቃ ግን መኮመኪያ ምክንያት አላጡም። እናም ሀድጎን ባገኙት ጊዜ ሁሉ ሀድጊ ብለው ነበር አሉ የሚጠሩት። አህያ ለማለት።ሀድጎም መረረውና ጃንሆይ ዘንድ ከሰሳቸው።. ንጉሱ አለቃን አስጠርተው ለምን ሀድጊ እያሉ እንደሚሳደቡ ቢጠይቋቸው አይ ጃንሆይ እኔ «አህያ ሸራህያ» እያልኩ ስጸልይ ሰምቶኝ እንጂ አልሰደብኩትም ብለው በብልሀት አመለጡ።

ጎመን እያበሰልሁ ነው 2. በእመቤታችን በፍስለታ ጾም አለቃ ቤተክርስቲያን አገልግለው ሲመለሱ ባለቤታቸው ማዘንጊያ የሚበላ ነገር በጎመን ይሰጧቸዋል ጎመኑ አልበስሎም ኑሮ ከምግብ በዃላ አለቃ ኆዳቸውን ወደሳቱ ጠጋ አድርገው ያሻሻሉ። ማዘንጊያ ነገሩ ገርሟቸው አለቃ ምን እያደረጉ ነው ይሏቸዋል አለቃም በአሽሙር ጎመኔን እያበሰልሁ ነው አሉ ይባላል።

አይ ጎራዴ አይ አስተጣጠቅ 3. አንድ የሚኒልክ መኮንን ስልብ ነበሩ ይባላል። መኮንኑ አንድ የጀግንነት ስራ ይሰሩና ሙሉ ትጥቅ ከነልብሱ ይሸለማሉ። አለቃን ያገኟቸውና “አለቃ እንዴት ነው?” “አላማረብኝም” ይላሉ።አለቃም መልሰው “አይ አስተታጠቅ አይ አለባበሥ አይ ጎራዴ አይ ጎራዴ አይ ጎራዴ” ይላሉ። ሌሎች መኳንንት መኮንኑን አለቃ ምን አሉህ? ይሉታል አደነቁኝ አይ አስተታጠቅ አይ ጎራዴ አሉኝ ይላል።መኳንንቱም ምን አደነቁህ ሰደቡህ እንጂ ስልብ ስለሆንክ ጎራዳ ነህ – አይ ጎራዴ -የኔ ጎራዳ ነው ያሉህ ብለው አብግነውት አለቃን ካልገደልኩ ብሎ በገላጋይ ነው አለቃ የተረፉት አሉ።

እንደምን አደራችሁ 4. አለቃ ሀሳባቸውን በሰምና ወርቅ በመግለጽ ጥበባቸው ተወዳዳሪ የላቸውም ይባላል። ታዲያ አንድ ቀን አንድ አውቃለሁ ባይ ሰውዬ ስለእርሳቸው ቅኔያዊ አነጋገር ምንም ቦታ እንደማይሰጥና በቅኔ ቢሰድቡት እርሱ ደግሞ ከዚያ በላይ በቅኔ መልሶ ሊሰድባቸው እንደሚችል ጉራውን ይነዛል። ጉራውንም የሰሙት ሰዎች አይ አንተ ሰው! ስለማታውቃቸው ይሆናል እንጂ የሚቻሉ አይደሉም። ይሰድቡሀል። ለማንኛውም ከፈለካቸው ወደገበያው መሄጃ መንገድ አከባቢ ስለማይታጡ ብቅ ማለት ትችላለህ ይሉታል። ሰውዬውም ቢያገኛቸው ለቅኔያቸው የሚሰጠውን መልስ እያሰላሰለ አህያውንም እየነዳ ወደ ገበያ ሲሄድ ያገኛቸዋል። ከዚያም ሰውዬው «አለቃ እንደምን አደሩ?» ይላቸዋል። አለቃም ትኩር አድርገው ያዩትና የተንኮል ሰላምታ መሆኑን በመረዳት «እግዚአብሄር ይመስጌን ደህና ነኝ! እናንተስ ደህና አደራችሁ ወይ?» ብለው በትህትና ለሰላምታው መልስ ሰጥተው ይሸኙታል። ሰውዬውም ስላልተሰደብኩኝ መስደብ የለብኝም ብሎ እየተኩራራ ይመለስና እነዚያን ሰዎች ያገኛቸዋል። ኧሃ ከአለቃ ጋር ተገናኛችሁ? ምንስ ብለው ሰደቡህ? ሲሉት እርሱም አይ ምንም አልሰደቡኝም እንዲያውም በትህትና ሰላምታ ተለዋወጥን። እኔን ሊሰድቡኝ አይችሉም ብያችሁ የለም? አለ። እስቲ እንዴት ነበር የተባባላችሁት ሲሉት አይ እኔ አለቃ እንዴት አደሩ ስላቸው እሳቸውም በትህትና አንገታቸውን ዝቅ አድርገው “እግዚአብሄር ይመስጌን እናንተስ እንዴት ናችሁ ነው” ያሉኝ አላቸው። ሰዎቹም ካንተ ጋር ሌላ ሰው ነበረ ወይ ሲሉት ኧረ የለም አህያዬን እየነዳሁ እሄድ የነበርኩ እኔ ብቻ ነበርኩኝ ሲላቸው አይ ወንድሜ ! አንድ ሰውማ እንዴት አደራችሁ አይባልም አንተን ከአህያህ ጋር አንድ አድርገው በመቁጠር ነው እንዴት አደራችሁ ያሏችሁ ብለው የሰውየውን መሸነፍ እና አህያ መባል አበሰሩለት አሉ።

እሱን ይጨርሱና (5) አለቃን አንዲት ጉብል ነች አሉ ያሸነፈቻቸው።ዝናዋን ይሰሙና ልጅቱዋ ቤት ሄድው አሳድሩኝ ይላሉ። ቤት ለእንግዳ ይባሉና እራትም በልተው የሚተኙበትን መደብ ጉብሊቱዋ ታሳያቸውና ትንሽ አጎዛ (የበግ /የፍየል ቆዳ) አምጥታ ትሰጣቸዋለች። አለቃም ይቺማ ታንሰኛለች ሌላ ጨምሪልኝ ይላሉ። ጉብሉዋም እሱን ይጨርሱና አክልሎታለሁ አለቻቸው አሉ።

አሸነፈቻቸው (6) እሩቅ አገር ሄደው መሽቶባቸው ከሚያውቋቸው ቤተሰብ ቤት ደርሰው አርፈዋል። ቤተሰቡም ካስተናገዳቸው በኋላ በይ መደቡ ላይ አንጥፊላቸው ብለው እናቱዋ ለልጂቱ ይነግሩዋታል። ልጅቷም የአንድ ትንሽ ፍየል አጎዛ ወስዳ ታነጥፍና ትመጣለች። አለቃ አንጥፌልዎታለሁና ሄደው ሊተኙ ይችላሉ ትላቸዋለች። ሄደው ሲመለከቱ አጎዛዋ እጅግ ትንሽ ከመሆኗ የተነሳ መደቡ መሐል ሆና አንሳ ትታያቸዋለች። ይሄኔ ይህች ድብዳብ እንድተኛባት መቼ ትበቃኛለች ይሏታል። ልጅቱም ስትመልስላቸው እሱን ከጨረሱ በኋላ እጨምርልዎታለሁ አለቻቸው ይባላል።

ሌላ እደግሞታለሁ (7) አለቃ ገብረ ሀና እጅግ በጣም ታዋቂና በነገር እንደማይሸነፉ በብዛት ሲወራ ሰምቻለሁ አንድ ወጣት ኮረዳ ግን እንዳሸንፈቻቸው ይነገራል እስቲ .. አለቃ ወደመንገድ ሲሂዱ ይመሽባቸውና ወደሰው ቤት ጎራ ብለው የመሸብኘ መንገደኛ ነኝ ብለው ይጠይቃሉ። ባለቤቶቹም ቤት ለንግዳ ብለው ያስገቧቸዋል። ምግብ በላልተው መኝታ ደረሰ። አለቃ አይናቸው ቁልጭ ቁልጭ ሲል ኮረዳዋ «አለቃ ምን ፈለጉ?» ስትላቸው ልጄ ጎኔን የማሳርፈበት ነገር አምጪልኝ አሏት። እሷም እሺ ብላ አንድ የበግ አጎዛ ሰጠቻቸው። እሳቸውም «ምነው ልጄ ይህቺ ትበቃኝ» ሲሏት፤ «እሷን ሲጨርሱ ሌላ እደግምዎታለሁ» አለች ይባላል።

እያሳራኝ ነው (8) አንድ ከዚህ በፊት የተረቡት ሰው መንገድ ላይ አግኝቷቸው ሊደብደብ ሲያባርራቸው እሳቸውም ሲሮጡ ቆይተው ሊደርስባቸው ሲሆን ቶሎ ብለው ሱሪያቸውን ፈተው ለመጸዳዳት ቁጭ ይላሉ። አለቃ በነበሩበት ዘመን ይትባሃሉ ሰው ጠላትም ቢሆን የሚገደለው፤ የሚደበደበው ከነሱሪው እንጂ ሱሪ አውልቆ አይደለም። ይሄ ወንድምነትም አያሰኝም። መለኛው አለቃ ይቺን ሰሩዋ። ሰውየውም ሊነርታቸው (ሊያሳራቸው) እስኪነሱ አጠገባቸው ቆሞ ይጠብቃል። እሳቸው ቁጭ እንዳሉ ሰውየው እንደቆመ ሁለቱን የሚያውቅ ሰው በመንገዱ ሲያልፍ ሰላም ብሏቸው የሁለቱ ነገር ገርሞት «ምን እያደረጋችሁ ነው?» ይላቸዋል። አለቃም ፈጠን ብለው «እያሳራኝ ነው።» ብለው መለሱ። ሊደበድባቸው የነበረው ሰውዬ በመልሳቸው ስቆ ትቷቸው ሄደ አሉ።

አለቃ ገብረ ሃና ሞቱ (9) አለቃ በጣም ቸገራቸውና ልጃቸውን ሂድና ንጉስ ሚኒሊክን አባቴ ሞቶ ግን ተስካሩን የማወጣበት ገንዘብ የለኝም ብለህ ገንዘብ ተቀብለህ ና ብለው ላኩት። ልጅም እንደተባለው ወደ ቤተመንግስት ሂዶ ያባቱን ከዚህ አለም በሞት መለየት ነግሮ እንደተባለው ገንዘቡን ይጠይቃል። ምኒሊክም እጅግ በጣም አዝነውና አልቅሰው ገንዘቡን ሰጥተው ይልኩታል። አለቃም ችግራቸውን ከተወጡ በኋላ ምኒሊክን ሊያዪ ጉዞ ወደ አ.አ. ያቀናሉ። በቤተመንግስቱም ያያቸው በመገረም እን…ዴ? አለቃ ሞተው አልነበር በማለት እየተገረሙ ለምኒሊክ ሊነግሩ ተጣደፉ። ሚኒሊክም ሲያዩአቸው ገብረሀና ሞተህም አልነበር ቢሏቸው አለቃም እንደርሶ የሚስማማኝ ንጉስ ባጣ ተመልሼ መጣሁ ብለው ንጉሱን አሳቋቸው አሉ።

አሬን ስበላ ከረምሁ (10) አለቃ የሚኖሩበት አካባቢ ድርቅ ጠንቶ ሁሉም ስደት ገባ።አለቃም ሲጓዙ ውለው ጥሩ አካባቢ ይደርሱና የግዜር መንገደኛ ነኝ ብለው አንዷን ባልቴት ለምነው ሊያድሩ ይፈቀድላቸዋል። ሌሊት ላይ ከመደባቸው ይነሱና ባልቴቱዋ ምኝታ ጋ ሄደው አይነ ምድራቸውን ተወጥተው ምኝታቸው ተመልሰው ባልቴቱዋን መጣራት ይጀምራሉ። ሴትየዋም «ምነው? ምን ሆኑ?» ስትላቸው ቤቱ አይነምድር አይነምድር ይሸታል እና መተኛት አቃተኝ ይላሉ። ሴትየዋም ኩራዟን ትለኩስና ፍለጋ ይጀመራል። አለቃም ተነስተው ወደ ባልቴቲቱ ምኝታ አካባቢ ሄደው እዚህ ነው እዚህ ነው ብለው ይጮሃሉ። «ኧረ ጉድ ኧረ ጉድ እንዴት ቤት ውስጥ ትጸዳጃለሽ ባይሆን እኔ አለሁ አይደል እንውጣ አትይኝም» ብለው ድምፃቸውን የበለጠ ከፍ ያደርጋሉ። ሴትየዋም ጎረቤት እንዳይሰማባት ብላ አለቃን ትለምናቸዋለች። ከዚያም ትንሽ አጉረምርመው አክርሚኝ ይላሉ። በዚህ ተስማምተው፤ አለቃም ከርመው ያ የድርቅ ወቅት ያልፍና ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የሚያውቃቸው ሰው አግኝቷቸው «እንዴት ከረሙ?» ይላቸዋል።አለቃም «አሬን ስበላ ከረምኩ» ብለው መለሱ አሉ።

አሬን ስበላ ከረምሁ (11) አለቃ ገ /ሀና ከጎንደር አዱ ገነት አፄ ምኒልክ መናገሻ ለደጅ ጥናት ሰንቀው በወረሀው ፆም አካባቢ ይጓዛሉ። ጥኌት ወደ ቤተ መንግስት የወጡ ማታ ወደ ማደሪያቸው እየተመላለሱ የወረሀውን ፆም ጨርሰው ፍስክ ሲገባ ወደ ጠጅ ቤቶች ጎራ እያሉ መልከስከስ ይጀምራሉ። የያዙት ደረቅ ስንቅ አልቆ ወደ ማርትሬዛቸው ምንዘራ ጀምረዋል። ወርሀ ግንቦት ገብቶ ክረምቱ ሊጀምር ሲል ውሳኔ ላይ መድረስ ነበረባቸው –ደጅ ጥናቱን ትተው ወደ ጎንደር ማቅናት ወይም እየተሟጠጠች ያለችውን ኪሳቸውን የሚያደልቡበት መንገድ መፈለግና ክረምቱን አራዳ ማሳለፍ፤ ደጅ ጥናቱንም መቀጠል። ታዲያ አንዷን የጠጅ ኮማሪት መሳም ከጀመሩ ቀኖች ተቆጥረዋል። አንድ ምሽት ግን ተንኮል አዘጋጅተው ኖሮ እሆን ብለው እዳሪያቸውን ሳይወጡ አብረው ይተኛሉ። ከሥራ በኌላ (ከመሳሳም በኌላ) እንቅልፍ መጥቶ የምኝታ ጓደኛቸውን እየረፈረፈ ሳለ፤ አለቃ ቀ .. ሰ . ስ ብለው ከጠፍር አልጋው እራቅ ብለው ይኮሱና ይዘውት ወደ አልጋው ቀ –ሰ –ስ ብለው ይጋደማሉ። ከዚያ የምኝታ ጓደኛቸውን (የጠጅ ቤቱን) ባለቤት መቀመጫ አካባቢ አብሰው የቀረውን ባካባቢው ያልከሰክሱታል። ሊቆዩ አስበው ሽታው ስላስቸገራቸው ሴትዮዋን መቀስቀስ ይገባሉ። ምነው ብለው ሲነቁ ሽታው እያድቀሰቀሰ የሚያመራው ወደሳቸው ጉያ መሆኑን የተገነዘቡ ኮማሪት። አለቃን። ስለፈጠረዎ በማሪያም ይዠወታለሁ። የሚፈልጉትን ሁሉ አደርጋለሁ። ከመሀላችን እንዳይወጣ ማለት። ደጅ ጥናቱንም ቢሆን እስከሚሳካልዎ እዚሁ ከኔ ጋር መቆየት ይችላሉ አሏቸው። አለቃም አይዞሽ ምንም ችግር የለም ያለ ነው። አትሰቀቂ ብለው ያረጋጓታል። በዚህ አስባብ አለቃ ወደ ጎንደር ሳይዘልቁ ክረምቱን ያለምንም ችግር ያሳልፋሉ።በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ አካባቢ ደጅ ጠኙ ሁሉ ምኒልክ ግብር ሲገባ እሳቸውም ይገኛሉ። በመገኘታቸው የተገረሙ አፄ ምኒልክም «እንዴ አለቃ እዚህ ምን ስትበላ ከረምህ?» ብለው ሲጠይቋቸው ህ ..ም ብለው «አሬን ስበላ ከረምሁ።» ብለው መመለሳቸውን ሰምቻለሁ።

አምባው ተሰበረ (12) አለቃ ድንግላዊ መነኩሴ ነበሩ። በእነ አለቃ ዘመን ወይዛዝርት መነኩሴዎችን ካሳቱ ለነሱ ወይ ለቤተሰቦቻቸው የግብር ምህረት ይደረግላቸዋል አሉ። እንደጀግናም ይወደሳሉ። ሰለዚህ መነኩሴን ለማሳት እና ለመገናኘት የማይደረግ ጥረት የማይፈነቀል ድንጋይ የማይቧጠጥ ዳገት የለም። እንደሚታወቀው የታቦት ንግስ ቀን ድግስ በየቦታው ይኖራል።ካህናትም ይጠራሉ ይባርካሉ ይበላሉ ይጠጣሉ።አንድ ቅዳሜ ቀን በዋለ ንግስ እለት የእነአለቃም የካህናት ቡድን ከቀትር በኋላ ወደእነማዘንጊያ ቤት ተጉዞ ሲበሉ ሲጠጡ ሲጫወቱ ውለው አመሻሹ ላይ ድንግላዊው መነኩሴ ገብረ ሃና መጠጥ አዳክሟቸው ኖሮ ካህናት ጓደኞቻቸው እና የማዘንጊያሽ ቤተሰብ ይስማሙና አለቃ እዚያው እንዲያድሩ ትተዋቸው ይሄዳሉ። አለቃም አደሩ። አዳራቸው ግን የወትሮው አልነበረም። ከማዘንጊያ ጋር ነበር። ማዘንጊያም እንደጎጃሞች አምባው ተሰበረ እንደነጅበላ ይፈር የነበረ አሉዋ። መነኩሴው ድንግልናቸውን አፈረሱ። በማግስቱ አለቃ አዝነው ወደ ሚያገለግሉበት ቤተ ክርስቲያን ሄደው የደረሰባቸውን ተናገሩ። ካህናቱም ምን ሲደረግ አሉ። አለቃም የእናንተስ ስራ ተገቢ ነው ጓደኛ ጥሎ መሄድ አሉ። አለቃና ማዘንጊያም ተጋቡ።

አለመመጣጠን (13)ማዘንጊያን ካገቡ በሁዋላ የቁመታቸው ያለመመጣጠን ችግር ፈጥሮባቸው ነበር ይባላል። አለቃ በጣም አጭር ማዘንጊያ በጣም ረጅም! ታዲያ ሲራ ሲጀምሩ ቢያንስ ከማዘንጊያ ግማሽ አካል በታች መውረድ ግዴታቸው ነበር። በስራ ወቅት መሳሳምም ሆነ ማውራት አይመቻቸውም። ስለዚህ ስራ ሊጀምሩ ሲሉ በይ ማዘንጊያ ደህና ሰንብቺ እኔ ወደ ቆላ መውረዴ ነው ብለው ይሰናበታሉ ይባላል።

አለቃ ወረኃና በጣም አጭር – ድንክዬ ሰው ናቸው (14)ሚስታቸው ወይዘሮ ማዘንጊያሽ ደግሞ ሲበዛ 1ሜትር ከ80 ናቸው። መንገድ ውለው ወደቤታቸው ሲመለሱ ወይዘሮ ማዘንጊያሽ ሠማዩን አይተው አለቃ ዝናብ ሊዘንብ ነው መሰለኝ ይሏቸዋል። ከዚያ አለቃ ከኋላቸው ኩስ ኩስ እያሉ ሲመልሱላቸው! «እኔ ምን አውቃለሁ ለሰማዩ ቅርቡ አንቺ ነሽ» አሏቸው ይባላል።

ገብተሽ አልቀሽ (15)አንድ ቀን ከወዳጃቸው ዘንድ ድግስ ተጠርተው ሄደው እዚያ ውለው ወደ ቤታቸው ሲመጡ አሽከራቸው በር ሲከፍት አስቀደመው አለቃ ገብተው የባለቤታቸውን መግባት ሲጠባበቁ ትንሽ ዘግየት ስላሉ «እባክሽ ገብተሽ ገብተሽ አልቀሽ እንደሆን በሬን ልዝጋበት» አሉ። የቁመታቸውን መርዘም መናገራቸው ነው።

ለሰማይ የምትቀርቢ (16)ወ /ሮ ማዘንጊያ የአለቃ የህግ ሚስት ረጅም ነበሩ። መንገድ አብረው ሲሄዱ ወ /ሮ ማዘንጊያ ወደ ሰማይ ያዩና «አለቃ ዝናብ የሚዘንብ ይመስሎታል ብለው ይጠይቃሉ»። አለቃም ሲመልሱ “ለሰማይ የምትቀርቢ አንቺ አይደልሽም እንዴ?” “እኔ ምኑን አውቀዋለሁ” ብለው ባለቤታቸውን በቁመታቸው ምክንያት ተረቧቸው።

እዚያም ቤት እሳት አለ (17)አለቃ የጎረቤት ፍቅር ይጀምሩና ባለቤታቸው ወ /ሮ ማዘንጊያ ዉኃ ሊቀዱ ሲወርዱ ጎረቢት ፍቅርን ልትቃመስ ትመጣለች። መጥታም ከአለቃ ጋር ሲንጎዳጎዱ ሳያስቡት ወ /ሮ ማዘንጊያ ቢደርሱባቸው ውሽምዬም ከመደንገጧ የተነሳ ልጅዋን ያነሳች መስሏት ያለቃን ልጅ አንጠልጥላ ትሮጣለች። ነገሩ የገባቸው ማዘንጊያም ልጁን አንስተው «አሁን እዚህ እሳት ውስጥ ልክተተው?» ቢሏቸው አለቃም ማዘንጊያ እዚያም ቤት እሳት አለ ብለው ልጁን አተረፉ አሉ። ከርታታ (Jun 11, 2005)

በጃቸው (18)አለቃ በጣም ሴሰኛ መሆናቸው ይነገራል። በአንድ ወቅት አንዲት ወጣት አይተዋት በመውደዳቸው ወላጆችዋን እንደምንም ብለው በማስፈቀድ ያገቧታል። አንሶላ የመጋፈፊያው ጊዜ ሲደርስ አለቃ ወረድ ብለው ስራ ሊጀምሩ ሲሉ እንትናቸው ተኝቶ አልነሳ እምቢ ይላቸዋል። ቢታገሉ ቢታገሉ አልተሳካላቸውም። ስለዚህ ሌላ አማራጭ በመውሰድ ለእጃቸው ተጨማሪ ስራ ሰጥተው ሲያሰሩ ያድራሉ። መከራዋን ስታይ ያደረች ልጅም ጠዋት ለሽንት እንደወጣች በዚያው ጠፍታ ወደ ወላጆችዋ ትሄዳለች። ችግሯን ግን ደፍራ አልነገረቻቸውም። ይሁንና አለቃ ሳያፍሩ ሽማግሌ ሰብስበው ወደ ልጂቱ ቤት ይመጣሉ። ሽምግልናም ይጀመራል። ለምን ትተሻቸው እንደመጣሽ፤ ምን እንደበደሉሽ ንገሪን ትባላለች። እንዴት ደፍራ ትናገር! ተቸገረች። በመጨረሻም ሲያዋክቧት ግራ ገባትና በእጃቸው …..ብላ የሚቀጥለውን መጨረስ ሳትችል ትቀራለች። አለቃም ምን ለማለት እንደፈለገች ይረዱና ወዲያውኑ ለሽማግሌዎች እስቲ እግዜር ያሳያችሁ! ድሮውንስ ላይበጀኝ ነው ያገባኋት በጃቸው የምትለኝ? ብለው ለጊዜው ጉዳቸው ሳይወጣ አሸንፈው ወሰዷት ይባላል።

ደርቆ ተንጣጣ (19)አንድ ሰሞን አለቃ በጣም ቆንጆ ልጅ ያገባሉ። ከዚያም ያው እንደ ባህል ወጉ ልጂቱ እሳቸው ጋ ልታድር ቤታቸው ትሄዳለች። እናም ቀኑ ተገባዶ ማታ ላይ አለቃ ቆጥ ላይ ወጥተው ሲጠብቋት እሷ ማታ ወደ ቤተሰቦቿ ከድታ ልትሮጥ ከቤት ስትወጣ ውጪው እንደአጋጣሚ ዝናባማ ስለነበር አድልጧት ትወድቅና ተመልሳ ቤት ትገባለች። ቤት ገብታም ምድጃ ዙሪያ ተቀምጣ ልብሷን ስታደርቅ ሳት ይላትና ጡጥ ታደርጋለች። ይህን የሰሙት አለቃ «አንቺ አትተኝም?» ይሏታል። እሷም «እስኪ ይቆዩ ልብሴ ምጥጥ ምጥጥ ይበልልኝ» ትላለች። እሳቸውም እሺ ብለም ዝም ሲሉ ልጂቱ አሁንም ደግማ ዛጥ ታደርጋለች።በሁኔታው የተቆጡት አለቃ በስጨት ብለው «አንቺ አትተኝም?» ሲሏት። እሷ «እስኪ ይቆዩ…ልብሴ ይድረቅ ትላለች።» ከዚያም አለቃ ቀጥለው «ኧረ …ኤዲያ …ልብስሽ ደርቆማ እየተንጣጣ» ብለው ባሽሙር ጠቅ አረጓት ይባላል።

እሷ ትታቀፋለች (20)የመሸባቸው መንገደኞች አለቃ ገብረሀና ቤት ምሽቱን ለማሳለፍ ይጠይቁና እንደ ባህሉ አለቃ “ቤት ለእንግዳ” ብለው ማደሪያ ይሰጧቸዋል። እንግዶቹም ፈረሶቻቸውን እደጅ አስረው ይገባሉ። አለቃንም «እባክዎ ፈረሶቹ እርቧቸዋልና ሳር ይስጡልን» ብለው ይጠይቃሉ። አለቃም «ምን ችግር አለ ታዲያ ከውጭ አጭጄ አመጣላቸዋለሁ» ይላሉ። ነገር ግን የአንዱ እንግዳ አይን ማዘንጊያ ላይ ሲቁለጨለጭ ያጤኑት አለቃ፤ ነገሩ ስላላማራቸው ማዘንጊያን ነይ እስቲ ተከተይኝ ይላሉ። እንግዶቹም«ለምን እሳቸውን (ማዘንጊያን) ያደክማሉ?» ብለው ይጠይቃሉ። አለቃም «አይደለም እኮ እንዲያው እኔ ሳጭድ እርሷ ትታቀፋለች ብዬ ነው» በማለት ስጋታቸውን በዘዴ ገለጹ።

ውዳሴ ማርያም ልደገም (21)አለቃ ገብረሀና የማይለመድ ለምደው ማታ ማታ ሰራተኛቸው ጋ ብቅ ሳይሉ አያድሩም ነበር። አንድ ቀን ሰራተኛቸው ጋ አምሽተው ቆይተው ቀስ ብለው ተደብቀው ገብተው ይተኛሉ። ትንሽ እንደቆዩ እንደገና ያምራቸውና ቀስ ብለው ምንም ሳያሰሙ እራቁታቸውን ሊሄዱ ሲነሱ ወ /ሮ ማዘንጊያ ነቄ አሉና «አንቱ ወዴት ኖት በዚህ በጭለማ» ብለው ወይዘሮ ማዘንጊያ ሲጠይቋቸው። «ቆዪ እስኪ አንዴ ውዳሴ ማርያም ደግሜ ልምጣ»አሉ። «ታዲያ ውዳሴ ማርያም እራቆት ተኩኖ ነው የሚደገም?» «ምን ላድርግ? እራቁቴን ሆኜ እንኳን ብትሰማኝ» ብለው እርፍ።

ቁጭ ብዬ ሳመሽ (22)ውሽምዬ አለቃ ሲወጡ ቤት ይመጣል እና ተማዘንጊያ ጋር ተላምደው ኖሯል።አለቃ ከውጭ ድክም ብሏቸው መጥተው ደጃፍ ያለች መደብ ላይ ቁጭ ብለዋል። ማዘንጊያም ከውሽምዬ ጋር የስንብት ሲሳሳሙ አለቃ አይተው ዝም ብለዋል። ውሽ…ም በጓሮ ተሸኝቶ ማዘንጊያ ወደ ደጃፍ ብቅ ሲሉ አለቃን ያዩዋቸዋል። «አለቃ መጥተዋል እንዴ?» ይላሉ። «እንዴ እዚህ ቁጭ ብዬ ሳመሽ አላየሽኝም እንዴ» ብለው ማዘንጊያ ሲሳሙ ማየታቸውን ተናገሩዋ። ታዲያ ይሙቱ እንዴ ታፍነው?

ጉድ ባይ ብዬ መጣሁ (23)አለቃ ከስራ በጣም ደክሟቸው ያለሰአት ወደ ቤት ይመጣሉ። ልክ እቤት እንደደረሱ ወ /ሮ ማዘንጊያ ሲያቃትቱ ሰምተው መቋሚያቸውን ጠበቅ አድርገው ወደ ቤት ሳያንኳኩ ..ሰተት ይላሉ ልክ እንደገቡ የሳቸው [የአለቃ] ቅርብ ጓደኛቸው አልጋቸው ላይ ከማዘንጊያ ጋር ጉዳዩን ተያይዞት ያያሉ። አለቃም ተገርመው «እና…ንተ» ቢልዋቸው። ማዘንጊያሽ እና ጓደኛቸው ደንግጠው «አለቃ ምነው ያለሰአቶ» ቢሏቸው እሳቸውም መልሰው «የስራ ባልደረቦቼን ጉድ ባይ ብዬ መጣሁ» አሉአቸው።

አስበጂና ላኪልኝ (24)የአለቃ ገብረሀና ጎረቤት የሆኑት አንዲት ወ /ሮ የአለቃን ባለቤት ወ /ሮ ማዘንጊያን ከአንድ ጎበዝ ጋር አስተዋውቃ ሁለቱ በየጊዜው ከቤቷ እየተገናኙ የልባቸውን ይወያያሉ። ከእለታት አንድ ቀን አለቃ ቤተ ክርስቲያን ተሳልመው ሲመለሱ ቤታቸው የፊጥኝ ታስሮና ተዘግቶ ስላገኙት ባለቤታቸው ወ /ሮ ማዘንጊያ ወዴት አንደሄዱ ጎረቤታቸውን ይጠይቋታል። እርሷም «መደብ እየሰራሁ ስለሆነ ማእዘኑን እያበጀችልኝ ነው» በማለት መልስ ትሰጣለች። እርሳቸውም “ቡና ስለጠማኝ ቶሎ አስበጅና ላኪልኝ” በማለት ትክክለኛውን መልእክት በዘዴ አስተላለፉ አሉ።

ማን ደፍሮ ይገባል (25)አለቃ ሚስታቸው የቂጥኝ በሽታ ይዟቸው ወሸባ ገብተው (የቤት ውስጥ ህክምና ) ከቤት ተኝተዋል። በሽታውን ማን እንዳስያዛቸው ሲመረመሩ ማንደፍሮ የሚባል የመንደር አውደልዳይ መሆኑን ሰምተዋል። ታዲያ አንድ ወዳጃቸው የሆነ ሰው «ኧረ ለመሆኑ ከርስዋ ቤት ማን ገብቶ ነው ሚስትዎን ቂጥኝ ያስያዛቸው?» ብሎ ቢጠይቃቸው «አዬ ወንድሜ ያስያዛትንማ ማን ብዬ ልንገርህ ከኔ ቤት ማን ደፍሮ ይገባል?» ብለው መለሱለት ያስያዛት ማንደፍሮ ነው ማለታቸው ነው።

ምልምሎች (26)ለእንጦጦ ማርያም ይመስለኛል ጣይቱ ለመዘምራንነት ድምጸ መረዋ የሆኑ ስልቦችን ለአገልጋይነት ይሰጣሉ። እነዚህ መዘምራን ከአለቃ ጋር በምን እንደተጣሉ አይታወቅም። አለቃ እነሱን እናንተ ምልምሎች ይሏቸዋል። መዘምራኑም ምኒልክ ዘንድ ይከሳሉ ተሰደብን ብለው። አለቃም ተጠርተው ሲጠየቁ አልተሳደብኩም ይላሉ። ከዚያ ምን ብሎ ነው አለቃ የሰደባችሁ ይላሉ ምኒልክ። መዘምራኑ አፍረው ዝም ሲሉ አለቃ ምን ትላለህ ይሏቸዋል። አለቃም አልተሳደብኩም እቴጌ ጣይቱ ከአገልጋዮቻቸው መካከል መርጠው መልምለው ለእንጦጦ ማርያም ስለሰጡ ነው ምልምሎች ያልኩት አሉ። ምኒልክም ስቀው ዝም አሉ አሉ።

ጭን እያነሱ መስጠት (27)የምኒልክ ወዳጅ የሆኑትን አለቃ በተረባቸው እትጌ ጣይቱ በጣም ይጠሏቸው ነበር አሉ። እናም አንድ ቀን በአል ነበር በአሉን ረሳሁት ለአለቃ እቴጌ አንድ የበሬ ንቃይ ይልኩላቸዋል። አንድ ጊደር ወይም ወይፈን የጠበቁት አለቃ በተላከላቸው የበሬ ንቃይ እግር (ጭን) ተናደው። «አይ እተጌ እንዲያው ለሰው ሁሉ አንዳንድ ጭን እያነሱ እየሰጡ ለምኒልክ ምን ሊተርፋቸው ነው? አይይ ኧረ ይሄን ለማንም እግር እያነሱ መስጠቱን ቢተውት ይሻላል።» ብለው በመናገራቸው ከምኒሊክ ቤተመንግስት ለመጨረሻ ጊዜ ተባረዋል።

ዋናውን ይዘው (28)አለቃ በቀልዳቸው በመወደድም ይሁን በመፈራት የሚፈልጉትን የማግኘት እድላቸው ሰፊ ነው ይባላል። በመሆኑም አንድ ለቤተመንግስት ሰዎች ቅርብ የሆኑ ታዋቂ እመቤት ቤት በእንግድነት ይገቡና በዚህም በዚያም ብለው በድብቅ ከእመቤቲቱ ጋር ወሲብ ይፈጽማሉ። ከዚያም ለካ ባልጠረጠሩበት መንገድ ሚስጥሩ ሾልኮ ቤተክርስቲያን ከባልደረቦቻቸው ጆሮ ገብቶ ባልደረቦቻቸውን አስቆጥቷቸዋል። አጅሬ ይህን ጉድ ሳይሰሙ እንደልማዳቸው ስራቸውን ሰርተው አድረው ጠዋት አገልግሎት ሊሰጡ ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄዱ ቀሳውስቱ ተመካክረው ከሴት ጋር አድረው መጥተው ቤተክርስቲያናችንን ሊያረክሱብን አይገባቸውም ብለው ሰድበው ያብርሯቸዋል። አለቃም ባጋጠማቸው ነገር አዝነው ከቤተክርስቲያኑ ይወጡና ካጥር ውጪ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብለው ዳዊታቸውን እየደገሙ ሳሉ እመቤቲቱ ፈረስ ላይ ቁጭ ብለው ከነአጃቢያቸው ይመጡና ከፈረሱ ወርደው ወደ ግቢ ያመራሉ። በዚህን ጊዜ አለቃ ብድግ ይሉና «በንጉስ አምላክ ይመለሱ! ወደ ውስጥ ሊያልፉ አይገባዎትም» ብለው ይጮሀሉ። ሰው ግራ ገብቶት «ምነው አለቃ ! ምን እያሉ ነው?» ሲል እሳቸውም ምንም የሌለው ምስኪን ካልተፈቀደለት እሳቸው ዋናውን ይዘው እንዴት ሊገቡ ይችላሉ?» በማለት ለሴትየዋ በሚገባ ዘዴ ተናግረው በማሳፈር መለሷቸው ይባላል።
Comment Box is loading comments...

Comments

Other posts you may likeወንዶች እስኪ መልሱ! Funny Gag
ወንዶች እስኪ መልሱ! Funny Ga...
picture
10283 views 15 likes
ወይኔ ማንቼ! Very Funny Gag
ወይኔ ማንቼ! Very Funny Ga...
picture
7184 views 4 likes
Top Funny Home Video Fails Compilation 2014
Top Funny Home Video F...
video
1854 views 1 likes
ሙቀቱ አልተቻለም Funny Gag
ሙቀቱ አልተቻለም Funny Gag
picture
7332 views 1 likes
ቁርጭምጭም ማለት ይሄ ነዉ  Monster Machine
ቁርጭምጭም ማለት ይሄ ነዉ Mons...
video
5190 views 6 likes
Father And His Babes Funny
Father And His Babes F...
video
7145 views 11 likes
Limote Newu Ende
Limote Newu Ende
picture
8373 views 13 likes
Amharic Joke Of The Day #93
Amharic Joke Of The Da...
picture
15752 views 6 likes
Funny Shop Kipper
Funny Shop Kipper
picture
5798 views 1 likes
Touching Amharic Story About Mother
Touching Amharic Story...
ahmaric-joke
25728 views 8 likes
Amharic Joke Of The Day Addisgag37
Amharic Joke Of The Da...
picture
34777 views 8 likes
Most Shocking And Amazing 18+
Most Shocking And Amaz...
video
7761 views 5 likes