የአለቃ ገብረሐና 71 ቀልዶች Part 2 -


Addis Gag is the only Ethiopian funny gag site 

እኔ ለነካሁት (29)አለቃ እንዲሁ ሴት ጋር ያድሩና ጠዋት ቤተክርስቲያን ሲሄዱ ይከለከላሉ እንዳይገቡ ያያቸው ሰው ስለነበር። እናማ በሴቶች በር በኩል ሄደው ዛሬ ሴቶች አይገቡም እዚህ ከገርገራው ውጪ ሆናችሁ ጸልዩ ብለው ሴቱን ሁሉ ከልክለው ካህናቱ ገርሟቸዋል አንድም ሴት ሳያዩ በመቅረታቸው። «ምን ሆነው ነው?» ሲሉ አንድ ያለቃን ስራ ያየ ካህን «አለቃ ከልክለው ነው ሴቶች እንዳይገቡ» ብሎ ያስረዳል።አለቃም ተጠርተው ሲጠየቁ «እኔ ለነካሁት ከተከለከልኩ እነሱ ይዘው እንዴት ይግቡ» ብዬ ነው አሉ።

መውጫችንን ነዋ (30)ቦታው የት እንደሆነ አላውቅም ብቻ ጣይቱ በእንጨት ደረጃ ወደ ፎቅ ይወጣሉ። ድሮ ያው ግልገል ሱሪ አልነበረም ፎቅ ሲወጡ አለቃ ደረጃው ስር ሆነው አንጋጥጠው የጣይቱን ምስጢር ያያሉ። ጣይቱም መለስ ብለው ወደታች ወደ አለቃ አዩና አለቃ «ምን እያዩ ነው?» ቢሏቸው። «መውጫችንን ነዋ» አሏቸው።

ኩኩሉ (31)መኳንንቱ በአለቃ ፍጥነት የሰላ አቃቂር ምን እናድርግ ብለው መከሩ። ነገ ሁላችንም እንቁላል ይዘን እንምጣና አለቃን እናፋጣቸው ብለው ተስማምተው በማግስቱ ጉባኤ ሁሉም ከኪሱ እንቁላሉን ብቅ ሲያደርግ አለቃም በቅጽበት እጃቸውን አርገፈገፉና ኩኩሉ አሉ። ከዚያም ለጥቀው ይህንን ሁሉ እንቁላል ያስወለድኩት እኔ ነኝ አሉ ይባላል። መኳንንቱ ሁሉ ሴት ዶሮ ሆነ።

በጠማማ ጣሳ (32)በአለቃ ተረብ በተደጋጋሚ ጥቃት ደርሶበት በቁጭት ላይ የነበረ ሰው እርሳቸውን የሚተርብበት ጥሩ አጋጣሚ በማግኘቱ እጅግ በጣም ደስ ይለዋል። ይሄውም አለቃ እሰው ቤት እንጀራ በምስር ወጥ ተጋብዘው እስኪጠግቡ ይበሉና በወጡ የተለቃለቀውን አፋቸውንም ሆነ ከንፈራቸውን ሳይታጠቡ ሰው ወደተሰበሰበበት አደባባይ ይመጣሉ። ሰውዬውም ያገኘውን አጋጣሚ በመጠቀም በሰው ፊት አዋርዷቸው ዝና ሊያገኝ በመጣደፍ፤ «አለቃ! በዛሬው ገበያ የምስር ዋጋ ምን ያህል ነበር?» ይላቸዋል። አለቃም የሰውየውን ተረብ በቅጽበት ይረዱና ቀና ብለው ሰውየውን ሲያዩት ጉንጩ በጣም የከሳና የተጣመመ መምሰሉን ይረዳሉ። ታዲያ ለሰውየው የሚሰጡት መልስ ምን መሰላችሁ። «አይ ልጄ! ምስርማ ዛሬ ተወዶ በጠማማ ጣሳ በብር አንድ ሲሸጥ ውሏል።» በማለት የጉንጩን መጣመም ጠቆም አድርገው ቆሽጡን አሳረሩት ይባላል።

አስደግፈውት አመለጡ (33)አለቃ መቼም ሲናገሩ ለነገ የለም እና አንዱን ዲያቆን አበሳጭተውት ሊደበድባቸው ይፈልጋቸዋል።እናም አንድ እለት በሩቅ ያዩትና ሮጠው እንደማያመልጡት ሲገባቸው ቶሎ ሮጥ ብለው አንድ ዘመም ወዳለ ጎጆ ይሄዱና ሊወድቅ ያለውን የጎጆውን ግድግዳ በጃቸው ደግፈው እንደቆሙ፤ ዲያቆኑ ይደርስባቸውና ምን እያደረጉ እንደሆነ ይጠይቃቸዋል። እሳቸውም ግድግዳው ሊወድቅ ስለሆነ ደግፈው መቆማቸውን እና እሱ ቢተካላቸው አጣና አምጥተው ግድግዳውን እንደሚያስደግፉ ነግረውት እሱ ሲተካላቸው አለቃ አስደግፈውት አመለጡዋ። አይ የያዛቸው ቀን እኔ የለሁበትም ቆርጦ ቆርጦ ነው የሚጥላቸው።

በሰው አገር ቀረሁ (34)አለቃ መንገድ ወጥተው ይመሽባቸውና የመሸበት እንግዳ ብለው ሰው ቤት ይጠጋሉ። በኋላም ያረፉባት ሴትዮ ያለቃን ተረብ ታውቅ ኖሮ ተጨንቃ ተጠባ አሳ ወጥ ሰርታ እራት ታቀርባለች። ያው ሴትየዋም አሳው ወጥ ላይ የማይገባበትን ውሀ ጨምራበት ነበርና ትንሽ ቀጠን ብሎ ነበር። ታዲያ አለቃም የቀርበላቸውን እራት ጥርግ አድርገው ከበሉ በኋላ ለቅሶ ይጀምራሉ። እንደው ያዙኝ ልቀቁኝ ሰዎቹም ተጨንቀው አረ አለቃ ምነካዎ? ብለው ቢጠይቁ «አዬ አሳ አገሩ ሲገባ እኔ በሰው አገር ቀረሁ» ብለው የሴትየዋን የአሳ ወጥ በደንብ አለመስራት ተናገሩ።

ከአልጋ ላይ ወድቄ ነው (35)አለቃ አንድ ቀን መንገድ መሽቶባቸው አንዲት ሴትዮ ቤት እንድታሳድራቸው ለምነው ቤት ለእንግዳ ብላ አስገባቻቸው። አለቃ ያው እንደሚተረከው ቅንዝራም ቢጤ ናቸው። እራት በልተው ከጨረሱ በኋላ በሉ እኔ መደብ ላይ እርሶ መሬት ላይ ተኙ ብላቸው ተኙ። ከዚያ ጨለማን ተገን በማድረግ ሴትየዋ መደብ ላይ ዘፍ ብላው መዳሰስ ይጀምራሉ። ሴትየዋም በድንጋጤ ነቅታ እንዴ ምን እየሰሩ ነው ስትላቸው ከአልጋ ላይ ወድቄ ነው አሏት። እንዴት መሬት ተኝተው ስትላቸው እኔንስ የገረመኝ እሱ አይደል አሏት ይባላል።

የተልባ ማሻው ሚካኤል (36)አለቃ ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር ሲመለሱ ያው የግድ የአባይን በረሀ ማቋረጥ ነበረባቸው። አብረዋቸው የነበሩ መንገደኞች በቃ የአባይ ሽፍታ ሊዘርፈን ነው ብለው ሲያለቃቅሱ። አለቃ ብራችሁን ሰብስቡና አምጡ ብለው – መንገድ ሲሄዱ ተልባ እየወቀጡ የሚበሉበት ሙቀጫ ውስጥ ብሩን በሙሉ ይጨምሩና አፉን ወትፈው፤ ሙቀጫውን የቤተ ክርስቲያን ጨርቅ አልብሰው ለአንዱ መንገደኛ እንደታቦት አሽክመው ሲጓዙ ሽፍቶቹ ዘንድ ይደርሳሉ። ሽፍቶቹም ብቅ ብቅ ይሉና «ምንድናችሁ?» ይላሉ። አለቃም ፈጠን ብለው «ታቦት ልናስገባ ይዘን የምንመጣ መንገደኞች ነን» ይላሉ። አንዱ ሽፍታም «የታቦቱ ስም ማን ነው?» ይላል። አለቃም «የተልባ ማሻው ሚካኤል ነው» ብለው መለሱ። ሽፍቶቹም ተሳልመው መንገደኞቹም በሰላም በረሀውን አለፉ።

ወላሂ ኑ እንብላ (37)አለቃ ከሩቅ ቦታ ወደ አገራቸው ሲመለሱ ሽፍቶች ሊደርሱባቸው ሲል ያላቸውን ገንዘብ አገልግል ውስጥ ከተው ጠበቁዋቸው። ለሽፍቶቹም ኑ እንብላ ወላሂ ጥሩ የዶሮ ወጥ ነው ቢሏቸው እኛ የእስላም ስጋ አንበላም ብለው ትተዋቸው ሔዱ ይባላል።

ግም ግም ሲል (38)ሊቁ ገብረሀና በሀያ ስድስት ዓመታቸው ጎንደር ውስጥ ሊቀ ካህናት ሆነው ተሾሙ። በዚህ ጊዜ አንዲት ጎንደሬ ዘንድ ጠበል ተጠርተው ቢሄዱ የሚወጡት ሰዎች ሁሉ «ጠላው ጥሩ አይደለም» ሲሉ ይሰሙና ተመልሰው ወደቤታቸው ይሄዳሉ። ሴትዮዋም በመቅረታቸው አዝና ቤታቸው ሄዳ «ምነው አባ ጠበል ጠርቼዎት ሳይመጡ ቀሩ?» ብትላቸው “ኧረ መጥቼ ሰው ግም ግም ሲል ጊዜ ነው የተመለስኩት።” አሏት።

ቢሻን እንበላለን ቢሻን እንጠጣለን (39)በሀገራችን እንደተለመደው ድግስ ካለ ቄሱም ሼሁም ሁሉም እንደየሀይማኖቱ ይጠራሉ። አዝማሪዎችም አይቀሩም። ስለዚህ የአለቃ ግዳጅ አንዱ ድግስ መሄድ ነው። ሴትየዋ ያው እንደነገሩ አሸር ባሸር የሆነ ድግስ ብጤ አድርጋ ኖሮ አለቃ ወጡም ቅጥንጥን ጠላውም ውሀ ውሀ ብሎባቸው ኖሯል። ደጋሽ መጥታ አለቃ ይብሉ እንጂ ትላለች። አለቃም «የመጣንበትን ቢሻን እንበላለን ቢሻን እንጠጣለን» ብለው የልባቸውን ተናገሩዋ ድግሱን የፈቀዱ መስለው።

ከመሶብዎ አይጡ (40)ሰው መቼም ወዶም ይሁን ፈርቶ አለቃን ይጋብዛቸዋል። አንድ ቀን ሊጋበዙ ወደ አንዱ ቤት ጎራ ብለው እንደተቀመጡ ጋባዥዋ ሴት እንጀራ ለማቅረብ መሶቡን ከፈት ስታደርገው ትንሽ አይጥ ዘላ ትወጣና ትሰወራለች። አለቃም ይህችን ጠንቀኛ አይጥ አይተዋት እንዳላዩ ጸጥ ብለዋል። ርቧቸው ስለነበረ ከራሳቸው ጋር እየታገሉ እስኪበቃቸው ድረስ ይበላሉ። ከዚያም በመጨረሻ ማእድ ሲነሳ መመረቅ የተለመደ በመሆኑ እንዲህ ብለው ይመርቃሉ ;- በላነው ጠጣነው ከእንጀራ ከወጡ እ /ር ይስጥልኝ ከመሶብዎ አይጡ።

የመጣሁበት ነው (41)አለቃ ገብረሀና አንድ ጣና ሀይቅ ላይ ካለ ደሴት ላይ የምትኖር ሴት ጸበል ቅመሱ ብላ ትጠራቸዋለች። አለቃም በጥሪው ቀን በጀልባ ተሳፍረው ከጥሪው ቦታ ይደርሳሉ። ነገር ግን ትንሽ አርፍደው ነበርና ብዙው ምግብ ቀድሞ በመጣው ተጋባዥ ተበልቶ ወደማለቁ በመቃረቡ ያለውን ወጥ እንደ ነገሩ ቀጠንጠን አድርጋ ነበር ሴትዮዋ ያቀረበችላቸው። ቢሆንም ግን አሁንም አሁንም ብቅ እያለች «አለቃ ይብሉ እንጂ» ትላለች። «እሺ….እሺ» ማለት የሰለቻቸው አለቃም በመጨረሻ እንዲህ ብለው ይመልሳሉ። «እንዴ እበላለሁ እንጂ ….ምናለ ይሄ እኮ የመጣሁበት ነው» ……… ውሀ ነው ለማለት ያክል።

ጠረር አርገሽ ቅጂው (42)አለቃ አንድ ቤት በእንግድነት ሄደው ሳለ ጠላ ይጋበዛሉ። ጋባዥ የነበረችው ሴትዮም ጠላውን ልትደግማቸው ጎንበስ ብላ ስትቅዳ ንፋስ ፈሷ ያመልጣታል። አለቃም ሰምተው እንዳልሰማ ይሆናሉ። የቀረበላቸውን ሲጨርሱ ሴትዮዋ እንደገና መጥታ «አለቃ ልድገሞት» ትላለች። አለቃም «ልድገም ብለሽ ነው? በይ እስቲ እንደቅድሙ ጠረር አርገሽ ቅጂው» ብለው መፍሳቷን እንዳወቁ በዘዴ ተናገሩ።

ዝግንትሉ ሞልቷል (43)አንድ ቀን አለቃ ግብዣ ተጠርተዉ ይሄዱና ምግብ ቀርቦ እየበሉ ሳለ ትል ያጋጥማቸዉና አኩርፈዉ እየበሉ ሳለ ጋባዡ በድንገት ይመጡና «ምነው አለቃ በደንብ ብሉ» ይሉዋቸዋል።አለቃም ተናደዉ ኖራልና «እሺ ጌቶች እየበላሁ ነው። ምን ጠፍቶ ዝግን ትሉ እንደሆን ሞልቷል።» አሉ ይባላል።

ጥፍር ያስቆረጥማል (44)አንድ ቀን አለቃ በእንግድነት ሰው ቤት ይሄዱና ምግብ ይቀርብላቸዋል። እየበሉ ሳለ በድንገት ከምግብ ጋር የገባ የጥፍር ቁራጭ ያገኙበታል። ከዚያም ባልቴቷም ትመጣና «አለቃ ብሉ እንጂ አይጣፍጥም እንዴ?» ትላቸዋለች።አለቃም የተቋጠረ ፊታቸውን ፈታ በማድረግ «ኧረ ይጣፍጣል ከመጣፈጥም አልፎ ጥፍር ያስቆረጥማል!!» አሉ አሉ።

የጓደኛህን ቀን ይስጥህ (45)አለቃ ገብረ ሀና ከሸዋ ወደ ጎንደር ግብዣ ተጠርተው ግብዣው ላይ ለመገኘት ይጓዙና ጎጃም ላይ ሲመሽባቸው ወደ አንድ ኮማሪት ቤት ይገቡና መጠጥ አዘው ቁጭ ይላሉ። አለቃ ደርባባዋ ኮማሪትዋ ቃ ትላቸውና እዛ ለማደር ያስባሉ። በጣም ሲመሽም ኮማሪትዋ ሌሎቹን ሰዎች ታስወጣና አለቃን አይታ እኚሕ ሽማግሌስ ምንም አያደርጉኝም ብላ ለሳቸው መደብ ላይ አንጥፋ ከጎናቸው ፈንጠር ብላ ትተኛለች። በነገራችን ላይ ሴትየዋ አንድ እግሯ የተቆረጠ እና በአርተፊሻል እግር ነበር የምትራመደው። አለቃም ለሊት ላይ ወደ ሴትየዋ ተጠግተው አሰስ ዳሰስ ማድረግ ሲጀምሩ ሴትየዋም ነቅታ በደህና እግሯ በርግጫ ብላ ትመታቸዋለች። አለቃም ቀበል ያደርጉና «የጓደኛህን ቀን ይስጥህ ሌላ ምን እላለሁ» ብለው እርፍ።

በቁሜ ቀምሼ መጣሁ (46)አለቃ ድግስ ተጠርተው አረፋፍደው ድግስ ቤቱ ቢደርሱ ሰዉ ሁሉ ተሳክሮ በብርሌ ሲፈነካከት ይደርሳሉ። ገና በሩን ገባ ከማለታቸው አንድ የተወረወረች ብርሌ ግንባራቸውን ትላቸዋለች። አይ ከዚህስ ቢቀርብኝ ይሻላል ብለው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ አንድ የሚያውቁትን ሰው መንገድ ላይ ያገኛሉ። ሰውየው «አለቃ ድግሱ እንዴት ነበር?» አለቃም «በጣም ቆንጆ ነበር። ቶሎ ሂድ እንዳያመልጥህ እኔ እንኳን አንድ በቁሜ ቀምሼ መጣሁ» ብለውት እርፍ።

ሺ ነዋ (47)አለቃ ገብረሃና አጤ ምኒልክ ግብር ሊበሉ ሄዱ። ተበልቶ ተጠጥቶ ለሽንት መውጣት አይፈቀድም ነበር። አለቃ ግን እወጣለሁ ብለው ተወራረዱ። ዘበኞች አናስወጣም ቢሏቸው «እምዬ ምኒልክ ለሽንት እንድወጣ ፈቅደውልኛል አሉ።» ዘበኞቹ «አይደረግም አሉ።» አለቃ «በሉ ንጉሱ ምን እንደሚሉ ስሙ አሉዋቸው።» ወደእምዬ ምኒልክ ጠጋ ብለው በጆሮዋቸው አንሾካሸኩ። «”500+500″ ስንት ይሆናል?” እምዬ ምኒሊክም ሂሳብ አይችሉም እንዳይባሉ ጮክ ብለው «ሺነዋ» አሉ። አለቃም «ሺነዋ (ሽናው ) ተብዬአለሁ» ብለው ወደሽንት ቤት ሄዱ።

ቡሊ የአለቃ አህያ (48)አንዴ አለቃ ቤት ጅብ ይገባና አህያቸው ቡሊ በፍርሀት ጩኸቱን ያቀልጠዋል። ሚስታቸው ማዘንጊያ አለቃን ቀስቅሰው ጅቡን እንዲያባርሩ ቢንግሯቸው «ባክሽ እኔ እፈራለሁ» በማለት አለቃ ሲመልሱ ማዘንጊያም ፈጠን ብለው «ኡኡቴ ለስሙ ነዋ ያንጠለጠሉት?» በማለት ይጠይቃሉ። አለቃም «ለማንጠልጠሉማ ቡሊ ይበልጠኝ አልነበር» በማለት መለሱ።

በጠማማ ቁና ሁለት ሁለት (1) (49)አለቃ ምግብ በተልባ በልተው አፋቸውን ሳያብሱ አደባባይ ወጥተዋል። አንዲት የተልባ ቅንጣት ወደ አገጫቸው ተለጥፋ ኖሯለች።አንድ ተጫዋች ወዳጃቸው አለቃ «ዛሬ ተልባ ስንት ስንት ዋለ?» ብሏቸዋል። አለቃም ገብቷቸው ስለነበረ ሰውየው የኔ ብጤ ውልግድግድ ያለ ስለነበረ «በቅፅበት በጠማማ ቁና ሁለት ሁለት ዋለ» አሉት አሉ።

በጠማማ ቁና ሶስት ሶስት (2) (50)አለቃ ገብረሀና የኢትዮጵያ ዘመናዊ ጥበበ ቀልድ /ኮሚዲ መስራች ሊባሉ ይገባል። አንዳንድ ተቺ ሰው አለ አይደል ዝም ብሎ መተቸት የሚወድ አይነት። አለቃ የበሉት ተልባ አፋቸው ላይ ሳይጠረግ አይቶ «ተልባ ገበያ ላይ እንዴት ዋለ?» ቢላቸው ሰውየው አፉም እግሩም የተጣመመ ስለነበር «በጠማማ ቁና ሶስት ብር ነበር።» አሉት።

አለቃ አለ ዕቃ (51)አንዴ አለቃ ገብረ ሀና መንደራቸው ካለ ግድግዳ ተጠግተው ሽንታቸውን እየሸኑ ሳለ ,አንድ ጎረቤታቸው አይቷቸው ሰላምታ ሊሰጥ «አለቃ» ቢላቸው እሳቸው «ቆሜ ስሸና እያየህ እንዴት አለቃ (= አለ እቃ ) ትለኛለህ» አሉት ይባላል።

ሰይጣኑ ይውለድህ (52)አለቃን አንዱ «ምነው ትንቦ ይጠጣሉ?» ቢላቸው። «ብጠጣው ምን አለበት?» አሉት። እሱም «ኧረ የሰይጣን ነው ይባላል። ስለዚህ ነውር ነው!» አላቸው። እሳቸውም ቀበል አድርገው «ሰይጣኑ ይውለድህና ያን ጊዜ ትከሰኛለህ! ለመሆኑ አንተ ለሰይጣኑ ምኑ ነህ?» አሉት ይባላል። (ምንጭ :- ቢልጮ 1948 ከአበበ አይቸህ )

በሌባ ጣትሽ አታሳዪኝ (53) አለቃ እጓሯቸው ዱባ ተክለዋል። ዱባውም አድጎ ፍሬ ይዟል። ፍሬውም ጎምርቶ (አሽቷል ) እሱንም ጧት ማታ እየተንከባከቡ ይጠብቃሉ። ከጎረቤታቸው አንዲት በሌብነት የሰለጠች ጋለሞታ ነበረች። አንድ ቀን ጧት ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄዱ አይታ ቀጥፋ ወሰደችባቸው። ሲመለሱ ዱባቸውን ያጡታል አዝነውና ተናደው ወይ ዱባዬ እያሉ ሲቃትቱ ያቺ አልማጭ ሌባ ከቤት ወጥታ «ምን ሆኑ አለቃ?» አለቻቸው። እሳቸውም «ዱባዬን ጉድ ሆንኩ ተሰረቅሁ» ይላሉ። እሷም ያዘነች በመምሰል ከንፈሯን እየመጠጠች የዱባው ፍሬ የነበረበትን ስፍራ በሌባ ጣታ እያመለከተች «አዎ አለቃ ትላንትና እዚህ ነበር እኔም አይቼዋለሁ» ስትል እሷ እንደሞጨለፈችው አውቀው «ተይው ልጄ በሌባ ጣትሽ አታሳዪኝ» ብለው ስርቆቷን ነገሯት።

አንቺ ባይበላሽ (1) (54)አለቃ ጠዋት ተነስተው ወጥተው፤ ስራ ውለው ለምሳ ሲመለሱ በጣም እርቧቸው ነበርና ምሳ እስከሚቀርብላቸው ይጠብቃሉ። ማዘንጊያ ሆዬ ለካስ ስራቸውን እየሰሩ ከአይቡም ጎረስ ሲያደርጉ ውለው ነበርና ምሳ ላይ ቸለል ብለዋል። አለቃም «ማዘንጊያ አትበይም» ብለው ቀና ሲሉ አፋቸው ላይ አይብ አይተዋል። «አይ ማዘንጊያ በይ ተይው አንች ባይበላሽ እኔ እበላዋለሁ» አሉ ይባላል።

አንቺ ባይበላሽ (2) (55)አለቃ አመሽተው እቤት ይመጣሉ ባለቤታቸው ቁጭ ብላ ፈትል ትፈትል ነበር። «እንደምን አመሹ አለቃ?» ትላለች «እኔስ ደህና ይላሉ»። ትንሽ ቆይታ እራት ታቀርባለች እንጀራ በሚጥሚጣ። አለቃም «ነይ ቅረቢ ይሏታል»። «አይ እኔ አልበላም ትላለች»። አለቃም «አይ አንች ባይብ በላሽ እኔ እበላዋለሁ» አሉ።

ቤቴ በየት ዞረህ መጣህ (56)እንግዲህ እሳቸው አያልቅባቸውም አይደል አንዴ ምን ሆኑ መሰላችሁ። ሚስታቸው ወይዘሮ ማዘንጊያ ነጋ ጠባ እንጀራ በተልባ እያቀረቡ ቢያስቸግሯቸው ጊዜ የተለየ ምግብ አላጣም ይሉና ቅምጣቸው ቤት ብቅ ይላሉ። ውሽማቸውም «ደህና መጡ» ትልና እንጀራ በተልባ ታቀርብላቸዋለች። ከዛ አለቃም በተራቸው ውሽሚት ሳትሰማ ዞር ብለው «ቤቴ በየት ዞረህ ቀደምከኝ ብለው እርፍ»።

መቋሚያዬን አቀብዪኝ (57)አንድ ቀን አለቃ ቀን ዘመድ ጥየቃ ውለው ሙቀቱ ድብን አድርጓቸው ድክም ብሏቸው ቤት ሲገቡ ባለቤታቸው ወይዘሮ ማዘንጊያ ወጥ እየሰሩ ይደርሳሉ። አሁን ገብተው አረፍ እንዳሉ ባለቤታቸውን መጠባበቅ ጀመሩ የሚበላ ነገር እንዲያቀርቡላቸው ግና ወ /ሮ ማዘንጊያ እየደጋገሙ ወጡን በማማሰያ ሲቀምሱ የታዘቡ አለቃ «ማዘንጊያ እንግዲህ እራታችን እሱ ከሆነ ለእኔም መቋሚያዬን አቀብዪኝ» ብለው እርፍ።

በየቀኑ ለጆሮ አዳዲስ የሆኑ ቀልዶችን ከ addisgag.com ብቻ!!!
Comment Box is loading comments...

Comments

Other posts you may likeTrue Dog Lover Ever Seen Funny
True Dog Lover Ever Se...
picture
6112 views 5 likes
የራስዋ አሮባት..funny Gag
የራስዋ አሮባት..funny Gag
picture
5243 views 4 likes
የማህፀን ኪራይ ክፍያ በ500ሺ ብር IN ETHIOPIA
የማህፀን ኪራይ ክፍያ በ500ሺ ብር...
joke
10748 views 2 likes
Best Barber Of The Year 2014 Funny
Best Barber Of The Yea...
picture
9325 views 3 likes
አውሮፕላን የሰራ ኢትዮጵያዊ ታዳጊ Amazing
አውሮፕላን የሰራ ኢትዮጵያዊ ታዳጊ ...
video
8320 views 46 likes
እቴጌ Funny Gag
እቴጌ Funny Gag
picture
10534 views 7 likes
Have You Ever Wear Your Shoe And Socks Till Become Like This? Funny
Have You Ever Wear You...
picture
7093 views 1 likes
Oppa Lej Yared Style
Oppa Lej Yared Style
picture
8253 views 4 likes
Kikiki Lol ሚስ ውሻ
Kikiki Lol ሚስ ውሻ
video
3903 views 3 likes
ቁርጥ አባባ ተስፋዬን Funny
ቁርጥ አባባ ተስፋዬን Funny
picture
5395 views 3 likes
ከተሞሸሩ አይቀር እንዲህ ነው Funny-wedding
ከተሞሸሩ አይቀር እንዲህ ነው Fun...
picture
9294 views 6 likes
እንደ አፍሽ ያድርገው Funny Gag
እንደ አፍሽ ያድርገው Funny Ga...
picture
6652 views 6 likes