አለቃ ገብረኃና All jokes 58-71 -


Addis Gag is the only Ethiopian funny gag site
ባዶ ሽሮ (58)ወራቱ ሁዳዴ ነው ታዲያ አለቃ ሲያስቀድሱ ውለው እቤት ይመለሳሉ። የአለቃን መምጣት ያዩት ማዘንጊያም ምሳ ለማቅረብ ተፍ ተፍ ይላሉ ታዲያ በዚህን ጊዜ አለቃ ከማዘንጊያ ደረት ላይ ተጣብቃ የቀረች አይብ ያያሉ። ትንሽ ቆይቶም ማዘንጊያ ባዶ ሽሮ ወጥ ይዘው ይቀርባሉ። አለቃም «በይ ነያ እንብላ?» ማዘንጊያም መልሰው «አይ እቴ ይቅርብኝ አላሰኘኝም።» አለቃም ማዘንጊያን ምሳቸውን አይብ እንደበሉ ገብቷቸው እንዲህ አሉ አሉ «በሁዳዴ ሽሮ እንዳይጥም አውቃለሁ አንቺ ባይበላሽ እኔ እበላዋለሁ»

ነዪ ብዪ እንጂ (59)ጾም ነው ሮቡዕ ቀን። አለቃ ጸሎት ከአጥር ግንብ ጎን ሆነው ይደግማሉ እንደገናም ወዴቤት እያሾለቁ ይመለከታሉ። ወይዘሮ ማዘንጊያ ወተት ንጠው ወተቱን አፍልተው አይብ ሠርተው እሱን ጎረስ ጎረስ ጎረስ በጤፍ እንጀራ ያደርጋሉ። አለቃ ይኼንን አይተዋል። ፀሎት አሣርገውወደ ቤት ይገባሉ ከሠዓት ላይ ነው። ለአለቃ ማዘንጊያ ቁርስም ምሣቸውን በማሰብ ምግብ በሽሮ ወጥ ያቀርቡላቸዋል። ይሔኔ አለቃ ማዘንጊያሽ «ነይ ብዪ እንጂ» ይሏቸዋል። ማዘንጊያም «አለቃ ምግብ አልበላ ብሎኛል ይሏቸዋል» ይሄኔ አለቃ «አንቺ ባይበላሽ እኔ እበላዋለሁ» ብለው ብቻቸውን ምሣቸውን በሉ ይባላል።

ገብርኤልና ሚካኤል ተታኮሱ (60)ወይዘሮ ማዘንጊያ ይፈሱና «ውይ ገብርኤልየ» ይላሉ። ይቆዩና እንደገና ይፈሳሉ «ውይ ሚካኤልየ» ይላሉ ከዛ ድንገት ዞር ሲሉ አለቃ ገብረሀናን በመስኮት ቆመው ያዩዋቸዋል። ድንግጥ ይሉና «እርሶ ደግሞ እዛ ቆመው ምን ያረጋሉ?» ብለው ይጠይቋቸዋል።አለቃ ገብረሀና ደግሞ «እን..ዴ.. ገብርኤልና ሚካኤል ሲታኮሱ እያየሁ ነዋ!» አሏቸው ይባላል።

ለምን ደወልሽው (61)አንድ ሴት ዉሀ ልትቀዳ ጎንበስ ስትል አንድ ጊዜ ያመልጣትና ድዉ ታደርገዋለች። ዘወር ብላ ስታይ አለቃ ገብረሀና ከኋላዋ ቆመዋል። ከዛም ደንገጥ ብላ «አለቃ ለመሆኑ ሰአት ስንት ሆነ ስትላቸው?» «አይ አንች ካላወቅሽዉ ለምን ደወልሽዉ?» አሏት ይባላል።

ቃታ መፈልቀቂያሽን (62)ሴትዮዋ ድምጽ ሳይሰማ ማስተንፈስ ፈለጉና በጣታቸው አንድ መቀመጫቸውን ከፈት አድርገው ቢለቁት ሳይሳካላቸው ቀርቶ ዱጥ ቢልባቸው ደንግጠው «ደራን ወጋው» ይሉና ዞር ሲሉ አለቃን ያዩዋቸዋል። ከዛም “አለቃ መቼ መጡ?” ብለው ቢጠይቋቸው «ደራ የተወጋ ጊዜ» ብለው ይመልሱላቸዋል። ሴትዮዋም በመደንገጥ «ምነው ጣቴን በቆረጠው?» ቢሉ አለቃም ቀበል አድርገው «ተይ እንጂ ምነው ቃታ መፈልቀቂያሽን» አሏት አሉ፡፡

ጠረር አድርገሽ ቅጂው (63)አለቃ አንድ ጊዜ መንደር ጠላ ቤት ይገቡና ሲጠጡ አሳላፊዋ አንዴ እሳቸው ጋር ስትደርስ የተፈጥሮ ነገር ሆኖ ፈስዋ ያመልጣትና ጠርር ታድርገዋለች እየቀዳች። ይህን የሰሙ አለቃ አንድ ጊዜ እሳቸው ጋር መጥታ «አለቃ ጠላ ልጨምርልዎት እንዴ?» ስትላቸው። «አዎዋ እስቲ እንደ ቅድሙ ጠረረ አድርገሽ ቅጂው» አሉ ይባላል።

አንድማ ግዙ (64)አለቃ ገብረሀና መሸት ሲል ጠላ ቤት ተቀምጠው ሲጠጡ ቆዩና ሽንት ለመክፈል በጓሮው በኩል ወጣ ብለው በሚሸኑበት ጊዜ ፈሳቸው ያመልጣቸውና ጡጥ ያደርጋሉ። ሰው ሰምቶ ይሆን ብለው ትንሽ ዞር ብለው ሲመለከቱ ኮማሪትዋም ትንሽ ራቅ ብላ እቃ እየፈለገች ኖራ ሰምታ ይሆናል ብለው በመስጋት አህያ እንደሚያባርሩ በመምሰል «ዙር !! ዙር !!» ብለው ሲጣሩ ሴትዮዋ ሰምታ «ኧረ! እኛ አህያ የለንም» ስትል አለቃ መልስ አይጠፋቸውም አይደል «አንድማ ግዙ» አሉ ይባላል።

በጠርር ሄጄ በታህሳሥሥ (65)አንድ ጊዜ አለቃ በመንገድ ላይ ከወዳጃቸው ጋር ሲሔዱ ወዳጃቸው ፈሱን መፍሳቱን ሰምተው ኖሮ ሰለነበር እንዴት እንደሚናገሩ እያስቡ ሳለ ድንገት ሰውየው «መቼ ነው ከከተማ የመጡት» ቢላቸው «በጠርርርር ……. ሄጄ በታህሳስስ …. ተመለስኩ» አሉ ይባላል። ሰውየን ማሰቀየም አልፈልጉም ማለት ይሆን?

መልግጌ አባስኩት (66)አለቃ ለቅሶ ሂደው ራት ከተበላ በኋላ ተጎዝጉዞ ከለቀስተኛ ጋር በመደዳ ይተኛሉ። ትንሽ ቆይቶ ፈሳቸው ይመጣባቸውና ቀስ ብለው ያለ ድምጽ ሊፈሱ አስበው ቂጣቸውን በጃቸው ከፍተው ቢለቁት ጠርር ብሎ ያሳፍራቸዋል። አለቃም አዝነው «አዬ መልግጌ አባስኩት» አሉ ይባላል።

ድንቼ (67)አንዲት አጠር ደልደል ያለች ደባካ መሳይ የኣለቃ ገብረሃና ጎረቤት ደግሞ «አባ ሰው ሁሉ ድንቼ የኔ ድንች እያለ ያቆላምጠኛል» ብትላቸው «አዮ ሞኝት እውነት መስሎሽ ነው?ድንቼ ድንቼ የሚሉሽ ሊልጡሽ እንጂ ነው» አሏት።

በነካ አፍህ (68)አለቃ ገብረሀና ከአንዱ ባለሱቅ ስውየ ጋር ማእድ ተቀምጠው ከተመገቡ በኋላ ስውየው የበላበትን እጁን ሲልስ አይተው ኖሮ «ወንድም በነካ አፍህ» ብለው እጃቸውን መቀሰራቸው ይነገራል።

ተኖረና ተሞተ (69)አንዲት እድሜ ልኩዋን በድህነት የኖረች አሮጊት በነ አለቃ ገብረሀና ሰፈር ውስጥ ታርፍና ሰው ለቀብር ጉድ ጉድ ሲልና ሲሯሯጥ ሲጣደፍ አለቃ በዚያው መንገድ ሲያልፉ “ምንድን ነው እጅብ እጅቡ” ብለው ይጠይቃሉ። “እንዴ አለቃ አልሰሙም እንዴ ?”፥ “ምኑን?”፥ “ያቺ ደሀ አሮጊት መሞቷን?”። አለቃም ቀጠል ያደርጉና “አሄሄ ተኖረና ተሞተ?” ብለው ተናገሩ። በህይወትም እያለች የቁም ሙት ሞታለች ያም ኑሮ ሆኖ ሞት ለሷም መጣባት ወይ እንደማለት ነው።

መሞትዎት ነው (70)አባ ገብርሀና የተዎለዱትና አርጅተው የሞቱት በጎንደር ክ /ሀ , ፎገራ ወረዳ ናበጋ ጊዮርጊስ የሚባል ገጠር ነበር። ክርስቶስ ሰምራ እየተባለ የሚታወቀው አካባቢ ማለት ነው። እናም ሰው መቼም ኑሮ ኑሮ መሞት አይቀርምና እሳቸውም ነፍሳቸው ልትወጣ እየተንፈራገጡ ሳለ (ሊሞቱ ማለት ነው) አንድ ከጎናቸው ተቀመጦ ጣረ ሞታቸውን ሲከታተል የነበረ ሽማግሌ አለቃን ጠርቶ «በቃ መሞትዎት ነው?» ብሎ ሲጠይቃቼው፣ «የግሚት ልጅ ታድያ ቆዳ እያለፋሁ መሰለህ» ብለውት እርፍ አሉ ይባላል።

የአለቃ የልጅ ልጅ (71)ነገሩ የሆነው ፎገራ ውስጥ ሲሆን በደርግ ዘመን ነው። ካድሬው ህዝቡን ሰብስቦ ስለ መንደር ምስረታ አስፈላጊነት ሲያብራራ «በመንደር ከሰፈራችሁ ውሃና መብራት በየቤታችሁ ይገባላችኋል» እያለ ከቀሰቀሰ በኋላ የህዝቡም ተቃውሞ አዳማጭ ሳያገኝ ሰፈሩ ሜዳ ላይ ተሰርቶ ሕዝብ ሰፈረ። ክረምት ሲመጣም ጣና ሐይቅ እንደተለመደው የፎገራን ሜዳ ቤቴ ብሎ ሲያጥለቀልቀው ህዝቡ ወደ በአካባቢው ከተሞች ተሰደደ። በዛን ወቅት የአለቃን የልጅ ልጅ ጋዜጠኛ አግኝቶ ስለ ሁኔታው ሲያነጋግረው «ያው በካድሬው እንደተነገረን ውሃው በየቤታችን ገብቷል መብራቱ ብቻ ነው የቀረው» ብሎ አስተያየቱን ሰጠ።
በየቀኑ ለጆሮ አዳዲስ የሆኑ ቀልዶችን ከ addisgag.com ብቻ!!!
Comment Box is loading comments...

Comments

Other posts you may likeTension Is Killing Me Funny
Tension Is Killing Me ...
picture
7945 views 4 likes
አዲስጋግ የእርሶና የቤተሰቦ መዝናኛ
አዲስጋግ የእርሶና የቤተሰቦ መዝናኛ
picture
7764 views 3 likes
እቴጌ Funny Gag
እቴጌ Funny Gag
picture
10480 views 7 likes
Jeky Chan In Ethiopia Funny Gag
Jeky Chan In Ethiopia ...
picture
12110 views 14 likes
ሱሴ Funny Gag
ሱሴ Funny Gag
picture
5929 views 3 likes
The Family Funny
The Family Funny
picture
1967 views 0 likes
ስለ አነዳዴ አስተያየት ይስጡኝ Funny
ስለ አነዳዴ አስተያየት ይስጡኝ Fu...
video
4693 views 7 likes
Awash Horrifying Car Accident
Awash Horrifying Car A...
gif
4657 views 0 likes
ምክር ቢጤ ለወንዶች Funny Gag
ምክር ቢጤ ለወንዶች Funny Gag
picture
8001 views 6 likes
I Phoneን ያሻሻለው ታዳጊ Funny
I Phoneን ያሻሻለው ታዳጊ Fun...
picture
5753 views 7 likes
Addis Gag Asgerami Zena
Addis Gag Asgerami Zen...
joke
15888 views 5 likes
ፎቶ ለመነሳት Funny
ፎቶ ለመነሳት Funny
picture
10824 views 2 likes