Traffic Police Ordered To Wear ዳይፐር - Amaric Joke


በፊሊፒንስ ትራፊኮች ዳይፐር እንዲያደርጉ ታዘዙ!

የሮማው ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ከጥር 7 እስከ 11 በፊሊፒንስ የሚያደርጉትን ጉብኝት በማስመልከት ትራፊክ ፖሊሶች ዳይፐር እንዲያደርጉ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ትራፊክ ፖሊሶች ዳይፐር እንዲያደርጉ ትዕዛዝ የተሰጠው በጳጳሱ ጉብኝት ወቅት ለረዥም ሰዓታት በሥራ ገበታቸው ላይ በተጠንቀቅ እንዲገኙ ታስቦ ነው፡፡ 

ዳይፐሩን ትራፊኮች ብቻ ሳይሆኑ የፀጥታ አስከባሪዎችም ጭምር የሚያደርጉ ሲሆን ይህም በጳጳሱ ጉብኝት ወቅት ፀጥታ አስከባሪዎቹም ሆኑ ትራፊኮች ለተፈጥሮ ጥሪ ወደ መፀዳጃ ቤት እንሂድ ሳይሉ በተጠንቀቅ ቦታቸው ላይ እንዲገኙ ዳይፐር ማድረጋቸው አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግሥት ኃላፊ ኤመርሰን ካርሎስ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡ ይህ ዕቅድ ከጳጳሱ ጉብኝት በፊት ቀደም ብሎ እንደሚሞከርም አስታውቀው ነበር፡፡ 

ጳጳሱ በአገሪቱ ከፍተኛ አድናቆት ስለሚሰጣቸው በጉብኝታቸው ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ እንደሚጠበቅ የገለጹት ኤመርሰን ‹‹የሕዝቡ ብዛት ከልክ በላይ ሊሆን ስለሚችል ዳይፐር እንሰጣቸዋለን›› ብለዋል፡፡ 

ይህ የመንግሥት ትራፊኮችንና የፀጥታ ኃይሎችን ዳይፐር የማስደረግ ፕላን በብዙዎች እንደ ቀልድ ታይቷል፡፡ ለትራፊክና ለፀጥታ አስከባሪዎች ጭምር ጉዳዩ እንደፌዝ ሆኗል፡፡

ምንጭ:- ትኩስ ወሬዎች እና ሌሎችም የፈስቡክ ገፅ!
Comment Box is loading comments...

Comments

Other posts you may likeአማርኛ Joke Of The Day #43
አማርኛ Joke Of The Day #...
picture
11155 views 1 likes
New Fashion For Pregnant Women Funny
New Fashion For Pregna...
picture
9319 views 2 likes
Meron Getnet Hagere Touching Potery
Meron Getnet Hagere To...
video
6988 views 8 likes
Vary Funny Kakaka
Vary Funny Kakaka
video
3676 views 5 likes
Jaguar Vs Crocodile Amazing
Jaguar Vs Crocodile Am...
video
5487 views 1 likes
Funny Car Air Bag In Africa
Funny Car Air Bag In A...
picture
2775 views 1 likes
እንዲህ ካለ አከራይ ይሰውራቹ Funny Gag
እንዲህ ካለ አከራይ ይሰውራቹ Fun...
picture
9833 views 7 likes
Message ለበአሉ Must See
Message ለበአሉ Must See
picture
16167 views 14 likes
የሃበሻ Men Must Learn From Him
የሃበሻ Men Must Learn Fr...
picture
5543 views 2 likes
Enen New
Enen New
picture
10769 views 32 likes
Funny ዓሳ ጎርጓሪ ምን ያወጣል አሉ
Funny ዓሳ ጎርጓሪ ምን ያወጣል ...
video
9894 views 4 likes
Caption The Pic Funny Gag
Caption The Pic Funny ...
picture
9645 views 3 likes