የተገላቢጦሽ! Amazing Zoo In China - Amaric Joke


የተገላቢጦሽ!

ወትሮው አደገኛ የሆኑ የዱር እንስሳት የሚጎበኙት እጅግ ጠንካራ በሆኑ የብረት አጥሮች ተወስነው አሊያም ለተመልካች ደህንነት አመቺ ከሆነ ርቀት ነበር።

በቻይና የሚገኘው ሌህ ሌዱ የተባለው የዱር እንስሳት መጠበቂያ ፓርክ የተገላቢጦሽ የሚመስል የጉብኝት መርሐግብር አዘጋጅቶ እየተገበረ ነው ይላል የኦዲቲ ሴንትራል ድረገጽ ዘገባ።

ቾንግኪንግ የተባለው ከተማ የዱር እንስሳት መጠበቂያ ፓርክ ሰዎችን በብረት በታጠረ መኪና በመያዝ ከተራቡ አንበሳዎችና ነብሮች ጋር ፊት ለፊት በማገጣጠም የሚያካሂደው አዲስ አይነት ጉብኝት ብዙ ተመልካቾችን ስቧል። ጉብኝቱ ሲካሄድ ከመኪናው የኋልኛ አካል ላይ ሙዳ ስጋ የሚንጠለጠል ሲሆን፤ ይህም እንስሳቱን ለመሳብ እና ወደ መኪናው እንዲቀርቡ ለማድረግ ነው።

በርካታ ሰዎች በብረት አጥሩ ተወስነው የእንስሳት መጠበቂያ ፓርኩን ለመጎብኘት በመጓጓታቸው ለመጪው ሶስት ወራት የተዘጋጀው ትኬት ተሽጦ ማለቁ የተገለጠ ሲሆን፤ የፓርኩ ቃል አቀባይ የሆኑት ቻን ሊያንግ ጉብኝቱ የታቀደበትን ምክንያት አስመልክተው እንዲህ ብለዋል « እኛ ለጎብኚዎቻችን ይህን አጋጣሚ ያመቻቸነው ምንም አደጋ ሳይከሰት እንስሳቱ ጥቃት ሲፈጽሙ የሚፈጠረውን ሁኔታ እንዲመለከቱ ነው።»

ከጎብኚዎቹ መካከል ታኦ ጄን የተባለው ሰው ከዚህ በፊት የዚህ አይነት ጉብኝት አለማየቱን ገልጾ «አስደናቂ ነው» በማለት ተናግሯል።

 
Comment Box is loading comments...

Comments

Other posts you may likeስኩል ባስ Very Funny Gag
ስኩል ባስ Very Funny Gag
picture
5959 views 5 likes
Funny Dish
Funny Dish
picture
5056 views 10 likes
Best አማርኛ Story Of The Day #18
Best አማርኛ Story Of The...
picture
12901 views 6 likes
Worlds Biggest Burger Black Bear Casino Amazing
Worlds Biggest Burger ...
ahmaric-joke
6898 views 2 likes
ያራዳ ልጅ  Vary Funny
ያራዳ ልጅ Vary Funny
picture
8561 views 11 likes
Picnic For X-Mas Funny
Picnic For X-Mas Funny
picture
6314 views 4 likes
Sometimes They Are Better
Sometimes They Are Bet...
picture
3790 views 1 likes
የተባረከ ባል A Blessed Husband Funny
የተባረከ ባል A Blessed Hus...
picture
9537 views 3 likes
እየነዱ እስክስታ Driving Esikesta Funny Ethiopian Driver
እየነዱ እስክስታ Driving Esi...
video
4531 views 2 likes
ቦክስ Kangaroo Vs Man
ቦክስ Kangaroo Vs Man
video
5770 views 3 likes
ጥንቆላ This Days Funny Gag
ጥንቆላ This Days Funny G...
picture
7950 views 2 likes
Ethiopian Migrant Boat, 70 Ethiopians Have Drowned
Ethiopian Migrant Boat...
ahmaric-joke
3298 views 1 likes