የመቶ ቀናት ምርጥ ቀልዶች - Amaric Joke


1. ስንኖር ዶሮ ስንሞት ዶሮ ወጥ እንሆናለን 2. አቢይ ከሚያመሽ ሚሰቴ አድራ ትምጣ 3. አቢይ አስመራ የሚያድረው እኛን ለማን ጥሎን ነው፤ ጅቦች ቢቢሉንስ፡፡ 4. እኔ አቢይን እንዳይገድሉት የምፈራው ለርሱ ብዬ አይደለም፤ እኔ እርሱ ውስጥ ነኝ የምፈራው እንዳይገድሉኝ ነው፡፡ 5. አቢይ እስር ቤቱን ባዶ አርገህ ምን ልታደርገው ቢሉት የቀን ጅቦች ላጉርበት አለ አሉ፡፡ 6. መለስ አባይን የደፈረ መሪ አቢይ አቦይን የደፈረ መሪ፡፡ 7. የመንግስት ሰራተኛ ነኝ። ዛሬ አንድ ጓደኛ ቤት ልደት ተጠርቼ ሄድሁ። የጓደኛ ልጅ አምስት ዓመቷ ነው። አምሽቼ ቤት ስደረስ ኢቲቪ ዜና ላይ ሁሉም አፍጧል። የሚታየው ዶክተሩ አስመራ ላይ "ግንቡን እናፈርሳለን " እያሉ እያወሩ ነው። የጓደኛዬ ልጅ ስትበር ወደ እኔ መጣች እኔም የገዛሁላትን ስጦታ አይታ መስሎኝ ደስ ብሎኝ ልስማት ዝቅ ስል አጅሪት " ጠቅላይ ሚንስትሩ ከተሾሙ ጀምሮ የምሰማቸው ግንቡን እናፈርሰዋለን ሲሉ ነው… ማነው ይሄን ሁሉ ግንብ የገነባው ብላ ጠየቀችኝ?" እኔም ለስጦታ የገዛሁትን ኬክ መሬት ላይ እያስቀመጥሁ በልቤ እንዲህ አልኋት" አንቺ የደረስሽበት የዐቢይን መንግስት ብቻ ነው እንደልብሽ ተናገሪ።" 8. አቢይ አህመድ እንደኛ የሰው ፍጡር መሆኑ ይጣራልን፤ እርሱ ያደረገውን ያደርግ ዘንድ ሰው አይቻለወውም፡፡ 9. ትናንታ ማታ ባለቤቴ እራት አቅርባ እየጠበቀችኝ እኔ ስልኬ ላይ ተጥጄ የጠቅላይ ሚኒስትሩ "አስመራ የቡና ቁርስ የሚያስቆርሱበትን ፎቶ "like"…"share" ሳደርግ ረጅም ጊዜ በመውስዴ ባለቤቴ በስጨት ብላ የቀረበውን እራት ማነሳሳት ጀመረች። ሳህን ሲንኳኳ ከስልኬ ቀና ብዬ " እራቱን አታንሺው እበላለሁ " አልኳት፡፡ እሷም" ምነው የጠቅላይ ሚንስትሩ ኩኪስ አላጠገበህም? ይልቁንስ ለኩኪሱ ማወራራጃ ውሃ ይሄውልህ" ብላ ፆሜን አሳደረችኝ። 10. አንዱ ዶክተር አቢይ አስመራ ቤተመንግስት የሚያስይዙትን ቡና ቁርስ እያየ ምንድነው ግን ትሪው ላይ ያለው ብሎ ጓደኛውን ቢጠይቀው ጓደኛው ፈጠን ብሎ….. እኔ ትሪው ላይ የሚታየኝ ወደብ ነው ብሎት እርፍ……. 11. የፓርላማ አባላት የዶክተር አቢይን ንግግር ከፍለው ነnው በነጻ ነው የሚሰሙት፡፡ 12. አንዱ ጓደኛውን ሰበር ዜና አልበዛብህም ቢለው….. እንዴ ሰውዬው እራሱ ሰበር ዝና ሀነብን እንጂ………… 13. እኚህ ሰውዬ በዚህ ችግሮችን እና እስረኞችን የመፍታት ነገራቸው ከቀጠሉ እኛንም ከሚስታችን እንዳያፋቱን አንድ ሊበሉ ይገባል 14. ጠሚው ለዞረው- እርሱ ለለፋው እኛ ደከመን እኮ፤ አቦ እንረፍበት አርሳቸውስ የሚደክሙ ጉድ አይደሉም፡፡ 15. አስቴር በዳኔ ትናንት "ከቤተመንግስት በግፍ ተባረርሁ" ብላ ሚዲያውን በአንድ እግሩ አቁማው መዋሏን የሰሙት የቀድሞዎቹ ቀዳማዊ እመቤቶች ወ/ሮ አዜብ እና ወ/ሮ ሮማን " እናቷ የሞተችበትና ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳሉ ''ብለው ተረቱ አሉ። "አሉ" ነው ያልሁት ። 16. ሰውየው ስራቸውንም ስራችንንም ጨረሱብን ምን እንስራ… ሚኒስትሮች 17. ሰውየው ጠሚውን እያማረሩ ይሳደባሉ- ያጉረመርማሉ- ይናደዳሉ፤ አንዱ ተጠግቶ ምን ሆነው ነው አባት ቢላቸው… ምን እሆናለው ይሄ ሰውዬ የት ከርሞ ነው እንዲህ መጫወቻ ሆነን ኖረን ዛሬ የመጣው ብለውት እርፍ…….. 18. አንዱ ኤርትራውያን ከወያኔ ጋር አሻጥር ሰርተው ፎርጅድ አቢይ መልሰውልን ቢሆነ ምን ዋስትና አለን ቢለው….. ወዳጁም ፈጠን ብሎ ነገ ጥዋት ሌላ ቦታ- ከሰአት ደግሞ ሌላ ቦታ ተገኝተ ተአምር ሲሰራ ካላየነው አውነትም ፎርጅዱ ነው የመጣው ማለት ነው……. 19. ለመሰረት ግንባታ ያሰቀመጥናቸውን ድንጋዮች እንኳን ገንብተን ሰብስበን አንጨርሳቸውም….. ደ/ር አቢይ አህመድ 20. " እውነት እውነት እላችኋለው ; ጅብ የሚያምርበት በጨለማ ነው ! ,,,በቀን ከመጣ ቀኑ ደርሷል ማለት ነው ! " 21. ጎበዝ ኤርትራውያን ምን አሉ መሰላችሁ አሰብ ወደብንና ቀይ ባህርን ኧረ ዛላንበሳንም ወሰዱና ዶ/ር አብይን ሰጡን አሉ፡፡ ምን ትላላችሁ 22. Hello Ras Teferians we have another God for you 23. በዚህ በለሊት ብቻዬን እያሳቀኝ ያለ ነገር፦ 24. ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ከአብይ ጋር የተፎካከረው እኮ ሺፈራው ሽጉጤ ነበር። አይ ሀገሬ!! 25. የሽግግር መሪ ስንጠብቅ የሽርሽር መሪ መጣብን 26. እንኳን ከደም መጣጭ መሪ ወደ ለጋሽ መሪ አሸጋገራችሁ 27. ከታገልክለት አብረኸው ትፈካለህ... ከታገልከው ግን ብቻህን ትረግፋለህ!! 28. ልክ ከከባድ ህመም ተነስቶ ወደ ውጭ እንደማይወጣ ሁሉ…ከቅዳሜው ሰልፍ በፊት በትንንሽ ሰልፎች መለማመዱ አይከፋም… ግርሻ እንዳይደፋን ወዳጄ!!! 29. "ሀ/ማርያም ግን ወርዶም ይሳሳታል?" "ምን አደረገህ ደሞ?" "ትዝ ይለኛል!!!" 30. "አባይ ፀሐዬ ኤቲኤም በካርድ አይደለም የሚጠቀመው…"እና በምንድነው?" "በቁልፍ ከፍቶ ነው የሚወስደው" 31. እኔ የምለው የአለም ዋንጫ ገና የምድብ ማጣሪያ ላይ አይደል እንዴ? ……እንጃ!! ኢቲቪ ግን የዋንጫውን እያሳየ ነው!! አቢይ እያጠቃ ነው!! 32. አረናዎች ሰላማዊ ሰልፍ ከማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ጋር ይምታታባቸዋል። ትንሽ ሰው ስለሚወጣ። እና አሽሟጣቾች ስማቸውን ቀይረውላቸዋል አሉ፦ "ኧረ-ና!!" 33. የመሪዎችን ፎቶ የሚሸጠውን ልጅ ለአምስተኛ ጊዜ፦"የመለስ ፎቶ አለህ?" "እንዴ! የለም እያልኩህ ለምንድነው እየደጋገምክ የምትጠይቀኝ?" "የለም ስትለኝ ደስ ይለኛል!!" 34. ጠሚው ከሳኡዲው ንጉስ ለሀገራቸው ረብጣ ዶላር ባገኙ ጊዜ አንዱ ምን አለ……. ሸቅበው ከሚበሉን …ሸቅለው ወደሚያበሉን!! 35. ሰውየው ሰው በመሆን ብቻ…ሰው እንዳልነበሩ አሳያቸው። 36. ከአሳቃቂ ወደ አነቃቂ !!Comment Box is loading comments...

Comments

Other posts you may likeVery Funny Facebook Gag
Very Funny Facebook Ga...
picture
13633 views 6 likes
Amazing Longest Crocodile Africa
Amazing Longest Crocod...
picture
6171 views 5 likes
Top 10 Funny Red Cards Ever
Top 10 Funny Red Cards...
video
2801 views 0 likes
መጥፋት አማረኝ Funny Gag
መጥፋት አማረኝ Funny Gag
picture
6920 views 3 likes
Cute Mother Cat  Funny
Cute Mother Cat Funny
picture
2956 views 0 likes
TOP 5 FUNNIEST MOMENTS - JOSE MOURINHO
TOP 5 FUNNIEST MOMENTS...
video
4498 views 1 likes
እንዲ ነው ሞተር መንዳት Very Funny
እንዲ ነው ሞተር መንዳት Very F...
video
7514 views 12 likes
Garden Style Very Funny Gag
Garden Style Very Funn...
picture
5470 views 2 likes
The Power Of Music Very Funny
The Power Of Music Ver...
video
4597 views 14 likes
ኧረ አስታራቂ የለም ወይ Very Funny Kid
ኧረ አስታራቂ የለም ወይ Very F...
picture
6672 views 1 likes
የመቶ ቀናት ምርጥ ቀልዶች
የመቶ ቀናት ምርጥ ቀልዶች
ahmaric-joke
6143 views 2 likes
Coming Soon In Addis Ababa
Coming Soon In Addis A...
picture
15651 views 18 likes